የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ማንችስተር ሲቲ ወሳኙን ሶስት ነጥብ አሳክቷል
የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ማንችስተር ሲቲተ ከመሪው አርሰናል ጋር ያደረገውን የሰላሳ ሶስተኛ ሳምንት የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር 4 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የአመቱን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል ።
ቤልጄማዊ አማካኝ ኬቨን ዴብሮይነ በጨዋታው 2 ግቦችን ሲያስቆጥር ጆን ስቶንስ እና ኤርሊንግ ሀላንድ ደግም የተቀሩትን ግቦች ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል ። የአርሰናልን ብቸኛ ግብ ሮብ ሆልዲንግ ማስቆጠር ችሏል ።
ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰባ ሶስት በማድረስ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ማጥበብ ችሏል።
በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከ ፉልሀም ጋር የሚገናኙ ሲሆን አርሰናል ደግሞ በለንደን ደርቢ ከ ቼልሲ ጋር ይጫወታል።
