ኢትዮጵያዊያን የደመቁበት የስፔን ሲቪላ ማራቶን
በ2023ቱ የስፔን ሲቪላ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል ።
በውድድሩ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በወንዶች ከ1 እስከ 3 ተከታትለው በመግባት ሲያጠናቅቁ ኢትዮጵያዊው አትሌት ጉዲሳ ሹሚ በ1ኛነት ውድድሩን አጠናቋል ።
አትሌት ከበደ ዋማ እና አትሌት መኳንንት አየው ደግሞ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል ።
የ 2023ቱ የስፔን ሲቪላ ማራቶን በሴቶችም ሲደረግ ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች አበሩ ሙሊሳ እና ኡርጌ ሸቦቃ ተከታትለው 2ኛ እና 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል ።