ቶተንሀም ወሳኙን 3 ነጥብ አሳክቷል ።
በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቶተንሀም ከ ዌስትሀም ዩናይትድ ጋር ባደረጉት ጨዋታ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ድል ቀንቶታል ።
የአንቶኒዮ ኮንቴውን ቡድን ቶተንሃምን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች ኤመርሰን ሮያል እና ሰን ሁንግ ሚን ከመረብ አሳርፈዋል ።
ቶተንሀም ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቡን 42 በማድረስ 4ተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
በቀጣይ ሊጉ መርሐ ግብር ቶተንሀም ከ ቼልሲ እንዲሁም ዌስትሀም ከ ኖቲንግሀም ፎረስት የሚገናኙ ይሆናል።