ቼልሲ በድጋሚ ሽንፈት ገጥሞታል ።

ቼልሲ በድጋሚ ሽንፈት ገጥሞታል ።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ በምዕራብ ለንደኑ ደርቢ ቼልሲ ከ ፉልሀም ጋር ያደረጉት ጨዋታ በፉልሃም አሸናፊነት 2 ለ1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል ።

የፉልሀምን የማሸነፊያ ግብ የቀድሞው የቼልሲ ተጫዋች ዊልያን እና ቪንሽየስ ሲያስቆጥሩ የቼልሲን ብቸኛ ግብ ካሊዶ ኩሊባሊ ከመረብ አሳርፏል ።

አዲሱ የቼልሲ ፈራሚ ጇ ፌሊክስ በመጀመሪያው የቼልሲ ጨዋታ ሜዳ ላይ አሪፍ እንቅስቃሴ ቢያደርግም በሰራው ድንገተኛ ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል ።

ቼልሲ በዚህ የውድድር አመት በሊጉ ሰባተኛ ሽንፈታቸውን ሲያስተናግዱ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ቼልሲ አንድ ቀሪ ጨዋታ ካለው ከሊጉ መሪ አርሰናል በአስራ ዘጠኝ ነጥብ ርቆ በሀያ አምስት ነጥብ 10 ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።

ፉልሀሞች በበኩላቸው በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አንድ ነጥብ ሰብስበው 6 ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቼልሲ ከክሪስታል ፓላስ እንዲሁም ፉልሀም ከኒውካስል ዩናይትድ የሚገናኙ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.