በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ወጣቶች ማዕከል የቴክኒካል ስብሰባ ተካሄደ

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ወጣቶች ማዕከል የቴክኒካል ስብሰባ ተካሄደ ፤

40ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድርን በተመለከተ ዛሬ ታህሳስ 22/2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሱሉልታ ከተማ በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ወጣቶች ማዕከል ከቀኑ 10:30 ላይ የቴክኒክ ስብሰባ ተካሄደ ።

ቴክኒካል ስብሰባውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድርና ተሳትፎ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አስፋው ዳኜ

የአትሌቲክስ ፋሲሊቲና ማህበራት አትሌቶች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት መሪ

የስልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሳሙኤል ብርሃኑ በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን ተሰብሳቢዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ስብሰባውን ያስጀመሩት ደግሞ የሱሉልታ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሽመልስ ነጋሽ ናቸው።

አቶ አስፋው ዳኜ ስለ ውድድሩ አላማ ፣ ስለ አሸናፊዎች የሚሰጠውን የሽልማት ፣ ስለ እድሜ ገደብ ፣ ስለ ውድድሩ አይነት እንዲሁም ስለ ተሳታፊዎች ብዛትና ስለ ተሳትፎ አይነት ጠለቅ ያለ ገለፃ አድርገዋል።

በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች እ.አ.አ ፌብሩዋሪ 18/2023 በአውስትራሊያ ባትረስት በሚካሄደው 44ኛው የአለም ሀገር አቋራጭ ውድድር ላይ እንደሚካፈሉ አቶ አስፋው አክለው ገልፀዋል።

ውድድሩ ነገ ታህሳስ 23/2015 ዓ.ም ከማለዳው 12:00 ጀምሮ ለተመልካቾች ክፍት እንደሚደረግ ሲገለፅ ከጠዋቱ 2:00 ላይ በድብልቅ ሪሌ በሱሉልታ ከተማ እንደሚጀመር ተገልጿል።

ምንጭ 👉የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

Leave a Reply

Your email address will not be published.