የ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታሀሳስ 22ቀን የተደረጉ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ አርሰናል መሪነቱን አስፍቷል

18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታሀሳስ 22ቀን 2015 የተደረጉ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ

 አርሴናል ከሜዳው ውጪ ወደ አሜክስ ስታዲየም ተጉዞ ብራይተንን በቡካዮ ሳካ ፣ ማርቲን ኦዴጋርድ ፣ ጋብሬል ማርቲኔሊ እና ኤዲ ኒኪታህ ባስቆጠሯቸው ግቦች 4ለ2 በማሸነፍ የሊጉ መሪነቱን በ7 ነጥብ ማስፋት ችሏል ።
ፈርጉሰን እና ሚቶማ ብራይተንን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች በሁለተኛ አጋማሽ አስቆጥረዋል ።

👉   ብራይተን 2-4 አርሰናል
⚽️ሚቶማ 65′    ⚽️ሳካ ‘2
⚽️ፈርጉሰን 77’ ⚽️ኦዴጋርድ ’39
⚽️ንኬቲያህ ’47
⚽️ማርቲኔሊ ’71

👉መድፈኞቹ አርባ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ከተከታያቸው ማንቸስተር ሲቲ በሰባት ነጥቦች ርቀው ሊጉን በበላይነት ተቆጣጥረዋል ።

👉በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል ከ ኒውካስትል እንዲሁም ብራይተን ከ ኤቨርተን የሚገናኙ ይሆናል።

👉የአርሰናል ተከታይና የአምናው የሊጉ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ባደረገው መርሐ ግብር ከኤቨርተን ጋር አንድ አቻ በሆነ ውጤት በማጠናቀቅ ነጥብ ጥለዋል።

ማንችስተር ሲቲ 1-1 ኤቨርተን
⚽️ ሃላንድ ’24            ⚽️ ግሬይ’64

👉የግብ አምራች የሆነው ኤርሊንግ ሀላንድ ሲቲን መሪ ቢያደረግም ዲማሪ ግሬይ ለኤቨርተን ግብ በማስቆጠር ክለቡን አቻ በማድረግ ለአርሰናሎችም ትልቅ እድል ከፍቷል።

👉በበተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ሌሎች የሊጉ መርሐ ግብሮች
ክሪስታል_ፓላስ እና ፉልሀም ሲያሸንፉ ኒውካስትል ከሊድስ ጋር አቻ ተለያይተዋል ።
ኒውካስትሎች ነጥብ መጣላቸውን ተከትሎ ከሲቲ ጋር በነጥብ እኩል የሚሆኑበትን እድል አበላሽተው ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

👉ፉልሃም 2-1 ሳውዛምፕተን
⚽️ ዋርድፕሮስ (በራሱ ግ) ዋርድፕራውስ’56
⚽️ ፓውሊኒሃ ’88

👉ቦርንማውዝ 0-2 ክሪስታል ፓላስ
⚽️አዩ ’19
⚽️ ኢዜ ’36

👉ኒውካስትል ዩናይትድ 0-0 ሊድስ

👉በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከ ቼልሲ እንዲሁም ኒውካስትል ከአርሰናል የሚጋጠሙ ይሆናል።

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.