ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ7ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ ።

የ7ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ የሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን አያገኙም።

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ7ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች በድሬደዋ አለም አቀፍ ስታዲየም ይካሄዳሉ። በፕሮግራሙ መሰረት ከታች ያለው መርሃ ግብር በድሬደዋ ተካሂዶ በቻን ውድድር ምክንያት ሊጉ ይቋረጣል ። ከ14ኛ ሳምንት በኋላ እና ሌሎች ተስተካካይ ጨዋታዎች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ቀጥለው የሚካሄዱ ይሆናል።

እሁድ ታህሳስ 16 2015
10:00 ሀድያ ሆሳዕና ከ ፋሲል ከነማ
01:00 አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

ሰኞ ታህሳስ 17 2015
10:00 ለገጣፎ ለገዳዲ ከ ወላይታ ድቻ
01:00 አርባምንጭ ከተማ ከ ባህር ዳር ከተማ

ከላይ የተጠቀሱት አራት ጨዋታዎች የሱፐር ስፖርት የውጪ ሀገር ባለሞያዎች የፈረንጆች ገና እና አዲስ አመት ለማክበር ወደ ሃገራቸው ስለሚመለሱ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደማይኖር ታውቋል።

ምንጭ👉ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

Leave a Reply

Your email address will not be published.