የሊዮኔል ሜሲ አስገራሚ ውጣውረዶቹና ክብር

ሊዮኔል ሜሲ  በአለም ዋንጫው ፍፃሜ ጎል በማስቆጠሩን በአለም ዋንጫ ፣ በቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ፣በአውሮፓ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ  ላይ ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያው አርጀቲናዊና የደቡብ አሜሪካዊ ተጫዋች ሲሆን በኳታሩ የአለም ዋንጫ ፍጻሜ ከ36 አመታት በኋላ ለአርጀቲና ዋንጫውን እንድታነሳ ከአጋሮቹ ጋር ታሪክ ሰርቷል።የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች በመባል ተመርጧል።

በአለም ዋንጫው በተጨማሪ ሰባት ጎሎችን በማግባት ከክልያን ምባፔን በአንድ ብቻ ተበልጦ ሁለተኛው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኗል ።በአጠቃላይ በእግር ኳስ ላይ በቆየባቸው ግዚያትም  ያስቆጠራቸው ጎሎች ብዛትም ሰባት መቶ ዘጠና ሶስት ማድረስ ችሏል።

👉ሜሲ በህይወቱ ያለፈባቸው አስቸጋሪ ውጣውረዶች

ትልቅ ስኬት ላይ ለመድረስ በመጀመሪያ አላማና ግብ ያስፈልጋል። ማለም ብቻም ሳይሆን ልናሳካዉ ለምንፈልገዉ ነገር በቁርጠኝነት መስራት ግድ ይለናል።

ሊዮኔል ሜሲ አሁን ያለበትን የስኬት ጫፍ ያልም ነበር። ይህን ለማሳካትም ጠንክሮ ሰርቷል። ፈተናዎችንም አሸንፎ ህልሙ ጋር መድረስ ችሏል።

ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ እንደ አዉሮፓዉያን አቆጣጠር ነሀሴ 24 1987 በአርጀንቲና ሮዛሪዮ ነዉ የተወለደዉ።

ገና በልጅነቱ በኳስ ፍቅር የወደቀዉ ሊዮኔል ሜሲ በ4 አመቱ ነዉ በሰፈሩ መንገዶችና ሜዳዎች ኳስ መጫዎት የጀመረዉ።

በከተማዉ በሚገኝ የህፃናት እግርኳስ አካዳሚን ተቀላቅሎ መጫወት ከጀመረ በኋላ የአሰልጣኞችና የሌሎች ተጫዋቾችን ቀልብ መግዛት ችሎ ነበር። ነገር ግን ለእግር ኳስ የሚሆን ተክለ ሰዉነት አልነበረዉም።

ነገር ግን ይህ ሜሲን ከወደፊት ህልሙ የሚያስቆመዉ አልሆነም።
በወር 1000 ዶላር እየተከፈለለት ህክምና ተደርጎለታል።

በ13 አመቱ ከአርጀንቲና ወደ ስፔን በማምራት የባርሴሎናን አካዳሚ የተቀላቀለ ሲሆን በዚህም ተክለ ሰዉነቱና ቁመቱ ፈታኝ ሆኖበት ነበር። ሜሲ ግን ምንም ፈተና ቢመጣበት በድል እንደሚወጣዉ ያምን ነበር።

ባርሴሎና ወጭዉን በመሸፈን ህክምና ተደርለታል።

የባርሴሎና ክለብ አመራሮችን በብቃቱ በማስደመም በ17 አመቱ ዋናዉን ቡድን በመቀላቀል እንደ ሮናልዲኒዮ ጎቾና ዣቪ ከመሳሰሉ ተጫዋቾች ጋር ተሰልፎ መጫወት ጀመረ። በምትሀተኛ እግሮቹ የእግር ኳስ አፍቃሪያንን ማስደነቅ የባርሴሎና ደጋፊዮችን ደግሞ በደስታ ማስፈንጠዙን ቀጠለ።

ሊዮኔል ሜሲ አብዛኛዉን የእግር ኳስ እድሜዉን ያሳለፈዉና ስኬታማ የእግር ኳስ ጊዜዉን ያጣጣመዉ በባርሴሎና ነዉ። የላሊጋና ቻምፒዮንስ ሊግን ጨምሮ በርካታ ዋንጫዎችን ከክለቡ ጋር አሳክቷል።

በርካታ ጎሎችን አስቆጥሯል። ሽልማቶችንም ወስዷል። በተለይም 7 ጊዜ የባሎንዶር ሽልማትን በመዉሰድ በአለም የእግር  ታሪክ የሚስተካከለዉ ተጫዋች የለም።

የቁመቱና የተክለ ሰዉነቱ ሁኔታ ሊዮኔል ሜሲን ከስኬቱ ሊያስቆሙት አልቻሉም።

ለሀገሩ አርጀንቲና ተሰልፎ በርካታ ጎሎችን አስቆጥሯል። በአለም ዋንጫ ለፍፃሜም ማድረስ ችሎ ነበር።

በአሁኑ ሰዓት 35 አመቱ የሆነዉ ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ አመሻሽ ላይ ይገኛል። ነገር ግን እግር ኳስ ከማቆሙ በፊት አንድ ሊያሳካዉ የሚፈልገዉ ነገር አለ። እሱም የአለም ዋንጫን ከሀገሩ አርጀንቲና ጋር ማንሳት ነዉ።

ይህን ለማሳካት በዘንድሮዉ የአለም ዋንጫ በአስደናቂ በራስ መተማመንና በጥሩ ስነልቦና ሌሎቹን የቡድን አጋሮቹን በመምራት ወደ መጨረሻዉ ምዕራፍ አድርሷቸዋል።

ያልተጠበቁ ዉጤቶች በተከሰቱበት የ2022 የኳታር አለም ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከሳዉዲ አረቢያ ጋር አድርጋ 2 ለ 0 ስትሸነፍ በርካቶች ከምድቧ ትወድቃለች እንጂ ለፍፃሜ ትደርሳለች ብለዉ በፍፁም አልገመቱም።

በተለይ የሳዉዲ ደጋፊዎች በማህበራዊ ሚዲያዉ ዌር where is messi (ሜሲ የታለ) እያሉ አሾፉበት።

ተዓምረኛዉ ሜሲ ግን ቀጣይ ጨዋታዎች ራሱንና ቡድኑን በማጠንከር በስነልቦና ለማሸነፍ ራሱን ዝግጁ አድርጎ ቀረበ።

ፖላንድና ሜክሲኮ 2 ለ 0 በማሸነፍ. . አንዳንድ ጊዜ ሽንፈት እንደሚያጋጥም ነገር ግን ጠንክሮ በመስራት ሽንፈትን መቀልበስ እንደሚቻል አርጀንቲናዎች አስመሰከሩ።

ከምድብ ጨዋታዎች በኋላ ወደ ሩብ ፍፃሜ ለማለፍ አዉስትራሊያን 2 ለ 1, በሩብ ፍፃሜ ኔዘርርላንድን በመለያ ምት በማሸነፍ, በግማሽ ፍፃሜ ክሮሺያን 3 ለ 0 በመርታት ለመጨረሻዉ ፍልሚያ ደረሱ።

በዚህ ሁሉ ጉዞ የአለም ምርጡና የ7 ጊዜ ባሎንዶር አሸናፊዉ ሊዮኔል ሜሲ ከዚህ በኋላ ሜሲ አርጅቷል የቀድሞ ብቃቱ አሁን የለም, where is messi (ሜሲ የታለ) ቢባልም ድንቅ ብቃቱና አስገራሚ ችሎታዉ ዛሬም ድረስ አብረዉት እንዳሉ አስመሰከረ።

በፍፃሜዉ ከአለም ሻምፒዮኖቹ ፈረንሳይ ጋር የሚገናኙ ሲሆን በርካቶች በጥረቱ አርጀንቲናን ለዚህ ላደረሰዉ ሊዮኔል ሜሲ እንዲያሸንፍና ዋንጫዉን ከሀገሩ ጋር እንዲያጣጥም ተመኝተዋል። ይህንንም አሳክቶታል።

ሜሲ በትጋት ከተሰራ ራስን መቀየር ብቻ ሳይሆን ለሀገር ኩራት መሆን እንደሚቻልም አስመሰክሯል።

እኛም በጠንካራ ስራና በትጋት ራሳችንን መለወጥ,ቤተሰቦቻችንን መርዳት, አለፍ ሲልም ሀገራችንን ማኩራትና ማስጠራት እንችላለን። በመንገዳችን ሽንፈት ቢያጋጥመን እንኳን ከስህተታችን ተምረን ለቀጣይ ድል መስራትና ማሸነፍ እንደሚቻል የሜሲዋ አርጀንቲና ምስክር ናት።

Leave a Reply

Your email address will not be published.