የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ2015 የውድድር ዘመን ነገ ይጀመራል

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ2015 የውድድር ዘመን ነገ ይጀመራል

የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ2015 የውድድር ዘመን ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች ጅማሮውን ሲያደርግ ጨዋታ በሚያስተናግዱ ከተሞችም የቅድመ ውድድር ስብሰባ ዛሬ ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ከበደ ወርቁ በሶዶ ከተማ የወላይታ ዞን አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድርን የሚመሩ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ አባላትን በማስተዋወቅ ስብሰባውን የጀመሩ ሲሆን የወላይታ ከተማ ውድድሩን በማስተናገድ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውጭ ውድድሩ በሰላም የተሳካ ሆኖ እንዲካሄድ እያደረጉ ላሉት እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስም ካመሰገኑ በኋላ በአቶ መኮንን ኩሩ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢነት ከሚመራው አብይ ኮሚቴ ሌላ በሶዶ ከተማ ሌሎች 4 ያህል ኮሚቴዎችም መቋቋማቸውን ተገልፆ የኮሚቴ አባላትም ትውውቅ ተካሄዷል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦችም ከዝግጅት ጀምሮ የተሻለ ነገር እንደተመለከቱ ሲገልፁ አቶ መኮንን በበኩላቸው ውድድሮች በህግ ብቻ ሳይሆን በመተሳሰብም ጭምር እንዲካሄዱ ፤ አላማው ተጫዋቾች ለብሄራዊ ቡድን እንዲበቁ ማድረግ በመሆኑ ክለቦች ሊያስቡበት ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊ ክለቦች ለተነሱ ጥያቄዎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ከበደ ወርቁ ምላሽ ሰጥተው ውድድሩም በሰላም እንዲጠናቀቅ ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማም የቅድመ ውድድር ስብሰባ የተከናከነ ሲሆን የሁለቱም ምድብ ጨዋታዎች በነገው ዕለት ጅማሯቸውን ያደርጋሉ።

የአንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር

ምድብ ሀ (ሶዶ)

እሁድ ታህሳስ 9

4:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢ/ስፖርት አካዳሚ
8:00 ወልቂጤ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
10:00 ባህርዳር ከተማ ከ ኢትዮ ንግድ ባንክ

ሰኞ ታህሳስ 10

8:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና
10:00 ቀይ ዛላ ከ አዲስ አበባ ከተማ

ምድብ ለ (አዲስ አበባ – አበበ ቢቂላ)

እሁድ ታህሳስ 9

8:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ፋሲል ከነማ
10:00 ሲዳማ ቡና ከ መቻል

ሰኞ ታህሳስ 10

8:00 አርባምንጭ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
10:00 አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

 

 

 

 

👉ዘገባው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.