አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ግማሽ ፍጻሜውን በመቀላቀል አፍሪካውያንና አረብ ሀገራትን አስፈንድቃለች።
አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ግማሽ ፍጻሜውን በመቀላቀል አፍሪካውያንና አረብ ሀገራትን አስፈንድቃለች።
በኳታር 2022 የአለም ዋንጫ ቅዳሜ ታህሳስ 1 ቀን 2015 ምሽት 12″ ሰአት የተከናወነ በሩብ ፍጻሜ ጨዋታ አሁን ሲጠናቀቅ አፍሪካዊቷ ሞሮኮ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ሀገር የሆነችውን ፖርቹጋል 1 ለ 0 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን በመቀላቀል አፍሪካውያንና አረብ ሀገራትን አስፈንድቃለች።
ፖርቱጋል 0-1 ሞሮኮ
አል-ኔስሪ 42′
ፖርቹጋል ብዙ ርቀት ትጓዛለች ተብላ ብትጠበቅም በአፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ከአለም ዋንጫ ዉጪ ሆናለች።
👉በአሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ የሚመራው የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በየሱፍ ኤል ነስሪ ብቸኛ ግብ ፖርቹጋልን በመርታት ግማሽ ፍፃሜውን በመቀላቀል ታላቅ ታሪክ ጽፈዋል።
የግማሽ ፍፃሜ የ አለም ዋንጫ ጨዋታ የመራ ዋሊድ ሬግራጉዊ የመጀመሪያው አፍሪካዊ አሰልጣኝ ግማሽ ፍፃሜም የተቀላቀለ የመጀመሪያው አፍሪካዊ አሰልጣኝ ሆኗል
አሰልጣኙ ከጨዋታው መጠናቀቅ በዃላም ይህንን ብለዋል።
” በድጋሚ ትልቅ ቡድን ቢገጥመንም ያገጣሙን ችግሮች ቢኖርም እስከ መጨረሻው ታግለን ታሪክ መፃፍ ነበረብን አፍሪካ ወደ ትልቁ መድረክ ተመልሳለች ” በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል
👉ሞሮኮ በምድብ ጨዋታ ያለፈችበት ውጤት
ሞሮኮና 0 – 0 ክሮሽያ
ቤልጂየም 0-2 ሞሮኮ
ሞሮኮ 2 – 1 ካናዳ
👉ሞሮኮ ከ16 ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ በተደረገ ጨዋታ
ሞሮኮ በመለያ ምት ስፔንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜ ተቀላቀለች።