የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ውጤት
የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ውጤት
የ2015 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ህዳር 25 ቀን ቀጥለው ውለዋል።
በምድብ ሀ 3 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ፖሊስ በኤርሚያስ ሙላት ጎል ሀዲያ ሌሞን 1-0 ሲያሸንፍ ዱከም ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማን ረድኤት እንግዳ እና ትንሳኤ አየለ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2-0 መርታት ችሏል። አሶሳ ከተማ ከ አዲስ አበባ ፖሊስ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ ያለ ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
በምድብ ለ 3 ሰዓት ላይ ኑዌር ዞን አረካ ከተማን በጀምስ ፑር ጎል 1-0 ሲያሸንፍ ቀጥሎ በተደረገው ጨዋታ ጎባ ከተማ ጌታሁን ኢርኮ ባስቆጠረው ጎል አዲስ ቅዳምን 1-0 አሸንፏል። አራዳ ክፍለ ከተማን የገጠመው ሀረር ከተማ 2-1 ማሸነፍ ሲችል ካሌብ ሀኪም እና አቡሽ መንግስቱ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
በምድብ ሐ 3 ላይ በተደረገው ጨዋታ ካራማራ ሀላባ ሸገርን 3-2 በሆነ ውጤት አሸንፏል። አብዱላዚዝ ሙሳ እና መሀመድ ሀሰን (2) ለካራማራ ሲያስቆጥሩ ለሀላባ ሸገር ወሰን ጌታቸው ሁለቱንም ጎሎች አስቆጥሯል። 5 ሰዓት ላይ አማራ ፖሊስ ከ ጎሬ ከተማ ያለ ጎል ጨዋታቸውን ሲያጠናቅቁ ቫርኔሮ ወ/13 ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጨዋታን አ/አ/ዩ በቸርነት ዓለማየሁ ሁለት ጎሎች 2-1 ማሸነፍ ችሏል። አንዋር ኑሩ ለቫርኔሮ አስቆጥሯል።
በምድብ መ 3 ሰዓት ላይ ደጋን ከተማ ከቤተል ድሪመርስ ያደረጉት ጨዋታ 1-1 ተጠናቋል። ቢላል ገመዳ በ 77ኛው ደቂቃ ለደጋን ሲያስቆጥር ማቲያስ ተሾመ በ44ኛው ደቂቃ ለቤተል አስቆጥሯል። 5 ሰዓት ላይ ሆምሻ ሻንጋን የገጠመው ሾኔ ከተማ 3-2 ማሸነፍ ችሏል። አንዷለም ሻሚቦ በ31ኛው ፣ ሽርሽር በላሶ በ69ኛው እና ዳግም ገረመው በ88ኛው ደቂቃ የሾኔን ጎሎች ሲያስቆጥሩ በሞጌ ፈረሰ እና መሐመድ አብዱልአዚዝ ለሆምሻ ሻንጋ አስቆጥረዋል። በ9 ሰዓት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ያደረጉት ጨዋታ ሰለሞን አለሙ በ18ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ 1-0 ማሸነፍ ችሏል።
ምንጭ 👉የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን