ጃፓን ታላቋን የእግርኳስ ሀገር ጀርመንን አሸነፈች

ጃፓን ታላቋን የእግርኳስ ሀገር ጀርመንን አሸነፈች

የአለም ዋንጫ 2022/ 2015
በኳታር ዶሀ

ዛሬ እሮብ ህዳር 14 2015 አ/ም(2022 እ.ኤ.አ) ምድብ አምስት ላይ በተከናወነ ጨዋታ ጃፓን ጀርመንን 2ለ1 አሸነፈች በዚሁ ምድብ ምሽት 1:00 ሰአት ስፔን ከ ኮስታሪካ የሚያደርጉት ጨዋታ እስከሚጠናቀቅ ጃፓን በመሪነት ጀርመን በውራነት ይቀጥላሉ ።

ለጀርመን ኢልካይ ጉንዶጋን በ33 ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሮ ጀርመንን መሪ ቢያደርግም ዶአን በ75ኛው እና አሳኖ በ83ኛው ደቂቃ ባስቆጠሩት ግብ ጃፓን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት እንድታሸንፍ አስችለዋታል ።

በቀጣይ የምድቡ ጨዋታ እሁድ ህዳር 18 ጃፓን ኮስታሪካን ስትገጥም ጅርመን ደግሞ ስፔንን ትገጥማለች ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.