የ2015 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በድምቀት ተከናወነ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በድምቀት ተከናወነ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ አማካኝነት በ1994 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን÷ በአፍሪካ ግንባር ቀዳምና ከአለም 6ኛ የጎዳና ላይ ሩጫ ለመሆን በቅቷል፡፡

በዛሬው እለት እሁድ ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም የተከናወነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ
መነሻው መስቀል አደባባይ ሆኖ በስቴዲዮም በኩል ወደ ሜክሲኮ አደባባይ፣ በባልቻ ሆስፒታል፣ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ በሰንጋተራ፣ በብሔራዊ ትያትር አድርጎ ወደ ካሳንችስ ቶታል፣ በኡራኤል አደባባይ ዞሮ መጨረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ ነበር።

40 ሺህ ተሳታፊዎችን ያስተናገደው ታላቁ ቁጫ በኢትዮጵያ ከዋናው የሩጫ ውድድር ቀደም ብሎም የአካል ጉዳተኞች ውድድር ተካሂዷል፡፡

ታዋቂ አትሌቶችን ጨምሮ ያሳተፈው ውድድር ከመጀመሩ በፊት በማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናኒሴ ጫሊ፣ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

በማስጀመሪያው ላይ አርቲስት ሀመልማል አበተ ከፌዴራል ማርሽ ቡድን ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር በማዘመር አስጀምረዋል።

በውድድር ላይ ከኢትዮጵያውያን ባሻገር የተለያዩ ሀገራት ዜጎች እና አትሌቶች በእንግድነትና በተወዳዳሪነት ተሳትፈዋል።
ኬንያዊቷ የረጅም ርቀት አትሌት ፔሬስ ጄፕቺርቺር እና የኬንያ የቀድሞ የረጅም ርቀት ሯጭ ሞሰስ ታኑይ በክብር እንግድነት እንዲሁም ሁለት የዩጋንዳ አትሌቶች ደግሞ በተወዳዳሪነት ተሳትፈዋል ።
የ22ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊዎች

በወንድች
👉 አንደኛ ከአማራ ማረሚያ ቤት አትሌት አቤ ጋሻው
👉2ኛ አትሌት ኃይለማርያም አማረ ከፌዴራል ማረሚያ
👉3ኛ አትሌት ገመቹ ዲዳ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ
በመሆን አጠናቀዋል ።

በሴቶች
👉1ኛ አትሌት ትግስት ከኦሮሚያ ደንና ጥበቃ ኢንስቲትዩት

👉2ኛ አትሌት መስታወት ፍቅር ከአዲስ አበባ ፖሊስ
👉3ኛ ፎቴን ተስፋዬ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.