አርጀንቲና ለአለም ዋንጫ ቅድመ ዝግጅት ጨዋታ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስን አሸነፈች

አርጀንቲና ለአለም ዋንጫ ቅድመ ዝግጅት የወዳጅነት ጨዋታ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ጋር አድርጋ 5 ለ 0 አሸንፋለች።

አልቫሬዝ 17′ ዲማሪያ በ25′, 36′

ሜሲ 44′ ኮሪያ 60′

የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ጎሎች አስቆጥረዋል።

አርጀንቲና በአለም ዋንጫዉ በግሩፕ C ነዉ የተደለደለችዉ

በዚህ ምድብ ሳዉዲ አረቢያ ሜክሲኮና ፖላንድ ይገኛሉ።

አርጀንቲና የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋን የምታደርገዉ ማክሰኞ ከሳዉዲ አረቢያ ጋር ነዉ።

ጀርመን ከኦማን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አድርገዋል ጀርመን 1 ለ 0 አሸንፋለች ።የጀርመንን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎል ፉልክሩግ ነዉ ያስቆጠረዉ።

ፉልክሩግ የዌርደር ብሬመን ክለብ ተጫዋች ነዉ።

ዌርደር ብሬመን በጀርመን ቡንደስሊጋ በ15 ጨዋታዎች 21 ነጥቦችን በመሰብሰብ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ከመሪዉ ባየር ሙኒክ ያላቸዉ የነጥብ ልዩነት 13 ነዉ።

የዚህ ክለብ ቁልፍ ተጫዋች ነዉ ፉልክሩግ

ጀርመን በኳታሩ የአለም ዋንጫ በGroup E ትገኛለች።

በዚሁ ምድብ የሚገኙት ደግሞ ስፔን ኮስታሪካና ጃፓን ናቸዉ።

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታዉን የሚያደርገዉ እሮብ ከጃፓን ጋር ይሆናል።

በሌላ የወዳጅነት ጨዋታ ስዊድን ሜክሲኮን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ጋና ስዊዘርላንድን 2 ለ 0 አሸንፋለች

Leave a Reply

Your email address will not be published.