በአሜሪካ በተካሄደ የ2022 ቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዉያን አሸነፉ
በአሜሪካ በተካሄደ የ2022 ቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊዉ አትሌት ፀጋዬ ኪዳኑ 2ተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።
የገባበት ሰዓት 1:02:10 ነዉ
በዚህ ዉድድር 1ኛ የወጣዉ ኬንያዊዉ ጂዎፍሬይ ኮች ሲሆን የገባበት ሰዓት 1:02:02 ነዉ።
ዞሄር ታልቢ 1:02:15 ሰዓት በማስመዝገብ 3ኛ ሁኖ አጠናቋል።
በሴቶች ቦሰና ሙላቴ 1:11:02 በሆነ ሰዓት በመጨረስ 1ኛ ሆና አጠናቃለች።
ኬንያዊያኑ ቪዮላ ቼፕጄኖና ቪቢያን ቼፕኪሩይ 2ኛና 3ኛ ሆነዉ ዉድድራቸዉን አጠናቀዋል።