በጀግናዋ ደራርቱ ቱሉ ስም ለተሰየመው ስፖርት አካዳሚ ድጋፍ ተደረገ !

በጀግናዋ ደራርቱ ቱሉ ስም ለተሰየመው ስፖርት አካዳሚ ድጋፍ ተደረገ !

በኦሮሚያ ክልል ሱሉልታ ከተማ ለተገነባው እና በረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ስም ለተሰየመው ስፖርት አካዳሚ አንድ መቶ አንሶላ ፣ አንድ መቶ ብርድ ልብስ፣ አንድ መቶ አልጋና አንድ መቶ ፍራሽ ለኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሳሚያ አብደላ ፣ የኦሮ/ወ/ስ/ቢሮ የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የኦሮሚያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊና ኢንስትራክተር ሽመልስ ዳዊት በተገኙበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ድጋፉን አስረክቧል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በርክክቡ ስነ ስርዓት ላይ እንዳሉት ይህን የመሠለ አካዳሚ በስማቸው በመሰየሙ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወሰነው ውሳኔ መሠረት ለአካዳሚው ይህን ድጋፍ በቦታው በመገኘት በማድረጋችን ደስታች ከፍ ያለ ሲሆን ይህን የመሠለ አካዳሚ ለአትሌቲክሱ እድገት መሠራቱ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል ሲል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዘግቧል።

የአካዳማው ህንፃዎቹ ግንባታም ማብራሪያ ተሰጥቷል

በ 22 ሁለት ሄክታር ላይ ያረፈ

1 ደረጃውን የጠበቀ የአትሌቲክስ ውድድር ማካሄድ የሚችል ትራክ

4 የቅርጫት ኳስ ሜዳዎች ያሉት

2 የእጅ ኳስ ሜዳዎች

6 የመረብ ኳስ ሜዳዎች

4 የቦክስ ሪንጎች

2 የመዋኛ ገንዳዎች

1 ደረጃውን ያሟላ ሁለ-ገብ ጂምናዝየም

9 ብሎኮች አንድ ሺ ስድስት መቶ ተማሪዎችን የሚያሳርፋ ህንፃዎች

80 አሰልጣኞችንና አስተማሪዎችን መያዝ የሚችል G+2 ህንፃዎች

1 ደረጃውን የጠበቀ ቤተ-መፅሐፍት፤

3 ካፍቴሪያዎችና የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ፤

በ2 ህንፃዎች ላይ 24 የመማሪያ ክፍሎች ያሉት፤

1 ክሊኒክ፤

3 የእግርኳስ ሜዳዎች ፤

1 አምፊ ትያትር ፤

1 የዳይሬክተርና አንድ የም/ዳ መኖሪያ ህንፃዎች ፤

1 ወርክሾፕ ፤

 

2 መጋዘኖች ፤

2 የሰልጣኞች ልብስ መቀየሪያ ህንፃዎች ፤

1 ትልቅ የአስተዳደር ህንፃ ያሉት ሲሆን በአጠቃላይ ከ13 በላይ ስፖርታዊ ውድድሮችን ማካሄድ የሚችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ ግንባታዎች መሆኑ ተገልጿል። ወ/ሮ ሳሚያ አካዳሚው በቅርቡ ተከፍቶ በይፋ ስራ እንደሚጀምርም ተናግረዋል ፌዴሬሽን አሳውቋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.