በስሎቬኒያ በተካሄደዉ የሉቢኒያ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን በሁለቱም ፆታዎች ድል ቀንቷቸዋል።

በስሎቬኒያ በተካሄደዉ የሉቢኒያ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን በሁለቱም ፆታዎች ድል ቀንቷቸዋል።

በወንዶች ገብረ ፃዲቅ አድሃና 2:06:09 በሆነ ሰዓት ዉድድሩን በመጨረስ ሲያሸንፍ ኤርትራዊዉ ሔኖክ ተስፋይ 2:07:12 የሆነ ሰዓት በማስመዝገብ 2ኛ ወጥቷል።

ኬንያዊዉ ላንጋት ሊዮናርድ 2:08:04 በሆነ ሰዓት በመግባት በሶስተኝነት አጠናቋል

ሌላኛዉ ኢትዮጵያዊ አብደላ ጎዳና 2:08:55 በሆነ ሰዓት በመግባት አራተኛ ሆኖ ውድድሩን ጨርሷል።

በሴቶች ስራነሽ ይርጋ 2:21:07 በማስመዝገብ ስታሸንፍ ስንታየሁ ለውጠኝ 2:22:35 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች።

ኬንያዊቷ ጃኔት 2:25:34 በሆነ ሰዓት በመግባት 3ኛ ሆና አጠናቃለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published.