መቻል ፋሲል ከነማን አሸነፈ
በአራተኛው ሳምንት የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ጠንካራውን ፋሲል ከነማ
በእስራኤል እሸቱ ጎል 1ለ0 አሸንፏል።
በቀጣይ በአምስተኛ ሳምንት መረሀ ግብር መቻል ከኢትዮጵያውያ መድን የሚጫወት ይሆናል።
ፋሲል ከነማ ሁለት ቀሪ ጨዋታዎች እያሉት በሁለት ጨዋታ ሶስት ነጥብ ያለው ሲሆን በቀጣይ
በአምስተኛ ሳምንት ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚጫወት ይሆናል።
ዛሬ በተከናወነ ሌላ የአራተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን በሲሞን ፒተር ጎል ወላይታ ድቻን 1ለ0 አሸንፏል።
በቀጣይ በአምስተኛ ሳምንት መርሀ ግብር ወላይታ ድቻ ከ ሀዲያ ሆሳዕና እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ከ መቻል ይጫወታሉ ።