ማንቸስተር ዩናይትዶች በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት ሽንፈትን ቀመሱ
በአዲስ አሠልጣኝ የመጀመሪያ ሽንፈት
ዛሬ በተደረገ የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሀግብር ማንቸስተር ዩናይትድ ብራይተንን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል ።
ጨዋታው በተጀመረ በ30ኛው ደቂቃ የብራይተኑ ፖስካል ግሮውዝ ግብ አስቆጥሮ ብራይተንን መሪ አደረገ ። ከ9 ደቂቃዎች ቆይታ በኋላ ራሱ ፓስካል ግሮውዝ ለራሱም ለክለቡም ሁለተኛ ግቡ አስቆጥሮ የመጀመሪያው አጋማሽ በብራይተን ሁለት ለ ዜሮ መሪነት እንዲጠናቀቅ አደረገ ።
ከእረፍት መልስ ወደ ጨዋታው ለመለስ የሞከሩት የአሠልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ማንቸስተር ዩናይትዶች ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በኋላ ከሽንፈት ያላዳነቻቸውን ግብ ማክአሊስተር በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሮ ጨዋታው በብራይተን ሁለት ለ አንድ አሸናፊነት ተጠናቋል ።
በአዲሱ አሰልጣኛቸው ኤሪክ ቴን ሀግ እየተመሩ የውድድር አመቱን የጀመሩት ማንቸስተር ዩናይትዶች የውድድር አመቱን በሜዳቸው ኦልድትራፎርድ በሽንፈት ጀምረውታል ።
አሠልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ በማንቸስተር ዩናይትድ ታሪክ በመጀመሪያው ጨዋታ በመሸነፍ ከአሠልጣኝ ዴቪድ ሞይስ በመቀጠል ሁለተኛው አሰልጣኝ ሆኗል ።
በአሠልጣኝ ግራህም ፖተር የሚመሩት ብራይተኖችም በበኩላቸው በውድድር አመቱ የሚኖራቸውን የቡድን ጥንካሬ አሳይተዋል ።
የማንቸስተር ዩናይትድ አዳዲሶቹ ፈራሚዋች ማርቲኔዝ እና ክርስቲያን ኤሪክሰን በቋሚ አሠላለፍ ውስጥ ሲያካትቱ ፖርቹጋላዊውን ኮኮብ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ከተጠባባቂ ወንበር እንዲጀምር አድርገውታል