በአፍሪካ ለመንገስ ሶስት ተጫዋቾች ተፋጠዋል
ካፍ የ2022 የአመቱ ምርጥ ተጫዋች የመጨረሻ ሶስት እጩዎቹን ይፋ ሲያደርግ ሳድዮ ማኔ ፣ ሞሀመድ ሳላህ እና ኤድዋርዶ ሜንዲ የመጨረሻ ሶስቱ ውስጥ የገቡ ተጫዋቾች ናቸው ።

የ2022 የውድድር ዓመቱን ከሊቨርፑል ጋር ያሳለፈው ሴኔጋላዊው የአጥቂ መስመር ተጫዋች በውድድር ዓመቱ ከክለቡ ሊቨርፑል ጋር የኤፍ ኤ ካፕ እና የካራባዎ ካፕን ማሸነፉ ይታወሳል ። ከሀገሩ ሴኔጋል ጋር ደግሞ የአፍሪካ ዋንጫ ማሳካት ችሏል ።

በእጩነት ከቀረቡት ሌላኛው ሴኔጋላዊ ኮኮብ አድዋርድ ሜንዲ በአፍሪካ ዋንጫው ልክ እንደ ሀገሩ ልጅ ሳድዮ ማኔ ቁልፋን ሚና በመጫወት ነው ሀገሩን ለአፍሪካ ዋንጫ ክብር ያበቃው ። ሜንዲ ከክለቡ ቼልሲ ጋር በመሆን የካራባዎ ካፕ እና የኤፍ ኤ ካፕ ላይ ለፍፃሜ ቢደርስም ሁለቱን በሊቨርፑል በመለያ ምት ተሸንፎ ዋንጫውን ሳያሳካ ቢቀርም ሀገሩ ሴኔጋል ወደ አለም ዋንጫው ስታልፍ ትልቁን ሚና ተጫውቷል ።
ሜንዲ ከክለቡ ከቼልሲ ጋር የአለም የክለቦች ዋንጫ እና የአውሮፓ ሱፐር ካፕን ማሸነፉም ይታወሳል ።

ግብፃዊው የሊቨርፑል አጥቂ መሀመድ ሳላህ ሌላኛው የካፍ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች እጩ ሲሆን በውድድር ዓመቱ ልክ እንደ ሳድዮ ማኔ ሁሉ የኤፍ ኤ ካፕ እና የካራባዎ ካፕን ከሊቨርፑል ጋር ማሸነፍ ችሏል ። መሀመድ ሳላህ በአፍሪካ ዋንጫው እና በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለፍፃሜ ቢደርስም ዋንጫዎቹንም ማሳካት አልቻለም ።

