መቋጫ ያላገኘው የክርስቲያኖ ሮናልዶ የዝውውር ጉዳይ
ፖርቹጋላዊው የ5 ባሎንዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከማንቸስተር ዩናይትድ የመውጣት ፍላጎት በኋላ በርካታ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ ።
የክርስቲያኖ ስም ከጀርመኑ ሀያል ቡድን ባየር ሙኒክ ጋር ቢያያዝም ባየር ሙኒኮች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የወደፊት እቅደዳቸው አለመሆኑን በይፋ ተናግረዋል ።
አሁን የሚወጡ በርካታ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የክርስቲያኖ ሮናልዶ የዝውውር ጉዳይ ከምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ጋር ተያይዟል ።
ከሳምንታት በፊት የክርስቲያኖ ሮናልዶ ወኪል የሆነው ሜንዴዝ ከአዲሱ የቼልሲ ባለቤት ቶድ ቦህሊ ጋር ተገናኝቶ መነጋገሩ ይታወሳል ።
ቼልሲዎችም አጥቂያቸውን ሮሜሎ ሉካኩን ለኢንተር ሚላን በውሰት አሳልፈው መስጠታቸውን ተከትሎ ክርስቲያኖ ሮናልዶን የማስፈረሙ ነገር በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ይሁንታን ያገኘ ነው ።
ታዲያ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ከማንቸስተር የመልቀቅ ፍላጎት ጋር ተያይዞ ማንቸስተር ዩናይትዶች በክርስቲያኖ ሽያጭ ላይ እስከ 15 ሚሊዮን ፓውንድ ድረስ እንደሚፈልጉ መረጃዎች ያሳያሉ።