ሻምፒዮን ለመሆን የሚደረገውን ፉክክር አጓጊ ያደረገው ጨዋታ።
▪️የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት የእለተ እሮብ ተጠባቂ መርሀ-ግብር 10 ሰአት ላይ ተካሂዷል።
▪️ፋሲል ከተማ 1-0 ቅ/ጊዮርጊስ
3’⚽️ ኦኪኪ አፎላቢ
▪️ከ60,000 በላይ ደጋፊዎች የታደሙበት እና መሪውን ከተከታዩ ያገናኘው ተጠባቂው መርሀ-ግብር በፋሲል ከነማ አሸናፊነት ተጠናቋል።
▪️ከ16ኛ ሳምንት በኋላ ምንም ግብ ያላስተናገደው ጠንካራው የቅ/ጊዮርጊስ የተከላካይ መስመር ጨዋታው ከተጀመረ ገና በ ሶስተኛው ደቂቃ ኦኪኪ አፎላቢ ባስቆጠረው ግብ ፋሲል ከተማ 1-0 በሆነ ውጤት ለእረፍት እየመሩ ወጥተዋል። ፋሲል ከተማ በጨዋታው በሙከራም ሆነ በጨዋታ እንቅስቃሴ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተሻሉ ነበሩ ማለት ይቻላል። ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ አልቻለም። ይህም የቅ/ጊዮርጊስ አለመረጋጋት እና የአእምሮ ዝግጁነት ጥያቄ ውስጥ የከተተ ነበር።

▪️በሁለተኛው አጋማሽ በቅ/ጊዮርጊስ በኩል አቤል ያለው እና ከነአን ማርክነህን ተክተው በማስገባት የማጥቃት እንቅስቃሴአቸውን ለማጠናከር ሞክረዋል። ጨዋታው ላይም ከቆሙ ኳሶች ወደ ጎል ለመድረስም ሞክረዋል። ግን የጨዋታውን ውጤት መቀየር አልቻሉም። የውድድር ዘመኑን የመጀመሪያ ሽንፈት አስተናግዷል።
▪️ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከተማ ነጥቡን 49 በማድረስ የነጥብ ልዩነቱን ወደ 5 አጥብቧል። ቅ/ ጊዮርጊስ በበኩሉ በ54 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ይገኛል።
▪️ከጨዋታው በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያያቸውን ሰጥተዋል።
▪️የቅ/ጊዮርጊስ ምክትል አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ 🗣በተጫዋቾቼ እንቅስቃሴ ደስተኛ ነኝ። እነሱ ጎሉን አስጠብቀው ለመውጣት ነበር የሞከሩት እግርኳስ ላይ የሚያጋጥም ነገር ስለሆነ ውጤቱን እቀበላለሁ ሲሉ
▪️የፋሲል ከተማው አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ በበኩሉ 🗣 በውጤቱ ደስተኛ ነኝ። የቤት ስራችንን ሰርተናል። ውጤት ለማስጠበቅ አልተጫወትንም ግን ጊዜው በሄደ ቁጥር ውጤቱን ማስጠበቅ ይኖርብሀል ተጫዋቾቼ ያንን አድርገዋል ፤ ተመልካቹን እንዲሁም ደጋፊዎቹንም እጅግ በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
▪️የሊጉ ጨዋታዎች ከሁለት ሳምንት በኋላ ሲመለሱ ቅ/ጊዮርጊስ ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ፋሲል ከተማ ከ ሰበታ ከተማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።
ሚካኤል ደጀኔ።
