የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ሻምፒዮን ቡድን ታውቋል።

▪️የ2014 የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር በዛሬው ዕለት በሰበታ ከተማ በደማቅ የመዝጊያ ስነስርዓት ፍፃሜውን አግኝቷል። አስቀድሞ የውድድሩ አሸናፊ የሆነው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በመዝጊያው ጨዋታ ሀላባ ከተማን 3-0 አሸንፎ ዋንጫ እና የወርቅ ሜዳልያውን የተረከበ ሲሆን ልደታ ክፍለ ከተማ የብር ፣ ሱሉልታ ከተማ የነሐስ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል። አራዳ ክፍለ ከተማ የውድድሩ የስፖርታዊ ጨዋነት ተሸላሚ ሲሆን የሰበታ ከተማ አስተዳደርም ውድድሩን በስኬት በማስተናገዱ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል። ለውድድሩ መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላትም የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.