አዳማ ከተማ አሰልጣኙን አሰናብቷል።

ያለፉትን አስር ጨዋታዎች በሊጉ ማሸነፍ ያልቻለው አዳማ ከተማ ከአሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር በስምምነት መለያየቱ ተገልጿል።

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከመጀመሩ በፊት አዳማ ከተማን በሁለት አመት ውል ለማሠልጠን ፊርማውን አኑሮ ቡድኑን የተረከበው አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በዝውውር መስኮቱ ራሱን በማጠናከር ውድድር ቢጀምርም እስከ 24ኛው ሳምንት ድረስ አራት ጨዋታዎች ብቻ ነው ቡድኑ ማሸነፍ የቻለው። በእንቅስቃሴ ደረጃ ብዙ የሚያስተቹ ችግሮች ባይስተዋልበትም ጨዋታን ከማሸነፍ ጋር ተያይዞ ክፍተቶች ይስተዋሉበት ነበር። በዚህም መሰረት ከትናንቱ የባህር ዳር ከተማ ሽንፈት ማግስት ከአሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር ለመነጋገር የተቀመጠው የክለቡ አመራርም በስምምነት መለያየታቸውን አሳውቋል።

▪️አዳማ ከተማ በሊጉ ከወራጅ ቀጠናው በ3 ነጥብ ርቆ በ27 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም የሊጉ መርሐ-ግብሩን በሳምንቱ መጨረሻ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ከሚገኘው ሰበታ ከተማ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.