የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የሚጀመርበት ቀን ተራዘመ።

▪️የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች በሀዋሳ ከተማ ጀምረው በባህርዳር መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ የሁለተኛውን ዙር ውድድር ደግሞ ከግንቦት 16 ጀምሮ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ለማድረግ ተወስኖ  ነበር።
ሆኖም የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻ የደርሶ መልስ ጨዋታውን ከናይጄሪያ ጋር የሚያከናውን በመሆኑ እንዲሁም ደግሞ የመካከለኛው እና ምስራቅ አፍሪካ ውድድር (የሴካፋ) ሴቶች ዋንጫ በዩጋንዳ ሲደረግ ሀገራችን ኢትዮጵያ ተሳታፊ በመሆኗ ቀኑ ማሻሻያ ተደርጎበታል። ሁኔታውን ከግንዛቤ በማስገባት በዛሬው ዕለት የፌዴሬሽኑ የበላይ አካላት ከክለብ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት መግባባት ላይ በመደረሱ ውድድሮች የሚገባደዱበትን ቀን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ፕሪምየር ሊጉ ሰኔ 11 እንዲጀመር በማለት ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

▪️አንዳንድ ክለቦች የተጫዋቾች ኮንትራት የሚጠናቀቀው ሰኔ 30 በመሆኑ እንዴት ሊሆን ነው በማለት ሀሳብ ያነሱ ቢሆንም ፌድሬሽኑ የውል ጊዜውም ቢያልፍ ሀገራዊ ጉዳይ ከመሆኑ አንፃር እና የተቀመጠ ደንብ በመኖሩ ተጫዋቾች ከውላቸው ውጪ ክለባቸውን እንዲያገለግሉ በማለት ተጨማሪ ውሳኔ ማስተላለፉን ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሚካኤል ደጀኔ

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.