ኤል ፒስቶሌሮ አትሌቲኮን ተሰናብቷል።
▪️ክለባቸውን በዚህ የውድድር ዘመን በኋላ የሚለቁ ተጫዋቾች ውስጥ ሌላው ልዊስ ሱዋሬዝ ነው። አትሌቲኮ ማድሪድ የዘንድሮው የውድድር ዘመን ሲጠናቀቅ ልዊስ ሱዋሬዝ ክለቡን እንደሚለቅ አትሌቲኮ ማድሪድ በትላንትናው እለት አስታውቋል።
▪️የ35 አመቱ ኡራጋዊ አጥቂ 2 አመት በስፔን ዋና ከተማ የቆየ ሲሆን አትሌቲኮ ማድሪድ ትላንት ከ ሲቭያ ጋር ጨዋታ ከማድረጋቸው በፊት ክለቡ አስታውቋል። ጨዋታውም ከተጠናቀቀ በኋላ ልዊስ ሱዋሬዝ እና ሜክሲኮአዊው ሄክተር ሄሬራ የአትሌቲኮ ማድሪድ ቀዩና ነጩን ደጋፊዎች ተሰናብተዋል። ሱዋሬዝ ጨዋታውን የጀመረ ሲሆን ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ተቀይሮ ሲወጣ ከደጋፊዎች ተኘስተው አጨብጭበውለታል።ከጨዋታው በኋላም ስሜታዊ የነበረው አጥቂ ተከታዩን ብሏል። “የአትሌቲኮ ደጋፊዎችን ፣ አሰልጣኞች ከመጣሁ አንስቶ ላደረጋችሁልኝ አቀባበል እና እንክብካቤ ሁሉንም በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ።ያለኝን 200% ሰጥቻለሁ አምና ሻምፒዮን ነበርን ከደጋፊዎቻችን ጋር ማክበር ባልችልም በየመንገዱ ሰዎች ለኔ የሚያሳዩኝ ድጋፍ እና አክብሮት ከልቤ አይጠፋም። ቤተሰቤ እና እኔ ምንጊዜም የአትሌቲኮ ደጋፊዎች ነን እናመሰግናለን ሲል በዋንዳ ሜትሮ ፖሊታኖ ላሉ ደጋፊዎች ሀሳቡን አጋርቷል። የአትሌቲኮ ማድሪድ ደጋፊዎችም “ሻምፒዮን ስላደረከን እናመሰግናለን” የሚል ባነር ይዘው ወደ ስቴዲየም ገብተው ምስጋናቸውን ገልፀዋል።
▪️ልዊስ ሱዋሬዝ ከባርሴሎና ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ በ2020 በነፃ ዝውውር ማቅናቱ የሚታወስ ነው። የዲዬጎ ሲሞኑን የአጨዋወት መንገድ ለመልመድ ጊዜ ያልፈጀበት ልዊስ ሱዋሬዝ አትሌቲኮ ማድሪድን ከ2014 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የስፔን ላሊጋን ሲያሸንፍ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል። 21 ጎሎችን በዛው የውድድር ዘመን ከመረብ ማሳረፍ ችሎ ነበር።
▪️የአምና ተፆእኖውን ዘንድሮ መድገም ያልቻለው ቋሚ 11 ላይ ብዙም የመሰለፍ እድል ያጣው ኡራጋዊው ኢንተርናሽናል አጥቂ በሁሉም ጨዋታዎች 13 ጎሎች እና 3 ኳሶችን አመቻችቶ ከማቀበል ግን ያገደው ነገር የለም። በቀጣይ ሳምንት አትሌቲኮ ማድሪድ ወደ ሪያል ሴጉሮስ አቅንቶ ሪያል ሶሲዳድን የሚገጥምበት ጨዋታ “የኤል ፒስቶሌሮ” የሚል ቅፆል ስም የወጣለት የልዊስ ሱዋሬዝ የመጨረሻ መርሀ-ግብር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ሚካኤል ደጀኔ።