ፊሊፕ ኩቲንሆ ዝውውር ቋሚ ሆኗል።
▪️በጥር የዝውውር መስኮት የካታላኑን ቡድን ባርሴሎናን ለ6 ወር በሚቆይ የውሰት ውል በመልቀቅ አስቶንቪላን የተቀላቀለው ፊሊፕ ኩቲንሆ አሁን በቋሚነት በቪላፓርክ የሚያቆየውን ውል ፈርሟል።
▪️አስቶንቪላ ለኩቲንሆ 20 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያወጣ ሲሆን የ29 አመቱ ብራዚሊያዊ ለ4 አመት በዌስት ሚድላንዱ ክለብ የሚያቆየውም ይሆናል።
▪️የአስቶንቪላው አሰልጣኝ ስቲቨን ጄራርድ በዝውውሩ በጣም ደስተኛ መሆኑን ገልፆ ኩቲንሆ ለቡድኑ ጥንካሬ አሰና ሚዛን እንዲጠብቅ ያደርጋል። ያን ደግሞ ከመጣ ጊዜ አንስቶ ሲያንፀባርቅ ተመልክተነዋል ሲል አስተያየቱን ገልጿል።
▪️የቀድሞ ክለቡ ባርሴሎና በማህበራዊ ትስስር ገፁ ክለባችን ስለነበረህ ቆይታ ከልብ ያመሰግንሀል ፤ በሄድክበት እንዲቀናህም ክለባችን ይመኛል ብለዋል። ፊሊፕ ኩቲንሆ እ.ኤ.አ በ2018 ጥር ወር ላይ ሊቨርፑልን በመልቀቅ በ146 ሚሊዮን ፓውንድ ባርሴሎናን መቀላቀሉ ይታወሳል።በቆይታው ካደረጋቸው 106 ጨዋታዎች 26 ጎሎችንም ከመረብ ማዋሀድ ችሏል።
ጥሩ ጊዜን በካምፕ ኑ አሳልፏል ማለት አይቻልም። የአሰልጣኞች መቀያየር እንዲሁም የወጣበትን ገንዘብ የማይመጥን እንቅስቃሴ የሚሉ ትችቶች አቅሙን በደንብ ለብሉግራናዎች እንዳያሳይ ያገደ ጉዳይ ነው። በ2019/20 የውድድር ዘመን በውሰት ውል በጀርመኑ ሀያል ክለብ ባየርሙኒክ ያሳለፈው ኩቲንሆ በ38 ጨዋታዎች 11 ጎል እንዲሁም 6 ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። በዛን አመት የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ማሳካቱ አይዘነጋም ታዲያ በሻምፒዮንስ ሊጉ ባየርሙኒክ ባርሴሎናን 8-2 ሲያሸንፍ ተቀይሮ በመግባት 2 ጎል ሲያስቆጥር 1 ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ባርሴሎና እ.ኤ.አ ከ1946 በኮፓ ዴል ሬ በሲቭያ 8-0 ከተሸነፉ ወዲህ በ1 ጨዋታ 8 ጎሎች አስተናግደው አያውቁም ነበር።
ሚካኤል ደጀኔ።