ኢትዮጵያን አረንጓዴ ጎርፍ ያሰኙና የተረሱ የቀድሞ አትሌቶች አስታዋሽ አገኙ።

ኢትዮጵያን አረንጓዴ ጎርፍ ያሰኙና የተረሱ አትሌቶች አስታዋሽ አገኙ።

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ አትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት እና የህብረት ባንክ የቀድሞ አስታዋሽ ያጡ ጀግና አትሌቶችን ለማገዝ የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሆቴል ተፈራረሙ።

የበጎ አድራጎቱ ድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን በቀለ በፊርማ ስነስርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር
👉በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ አትሌቲክስ አርማችን ነው የኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲውለበለብ በአለማችን ላይ ሰሟ እንዲጠራ ካስቻሉ አንዱና ዋነኛው አትሌቲክስ ነው ይህን አትሌቲክስ የመጠበቅ የመንከባከብና ታላቅ ስራ ያከናወኑትን ጀግኖች ደግሞ መደገፍ አስፈላጊ ነው ብሎ የተቋቋመ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ከሚያከናውናቸው ተግባር ውስጥ አንዱ የግንኙነት ጊዜን ማመቻቸት ፣ማእድ ማጋራት ፣ለበዓል ድጋፍ የምንሰጥበት 2ኛ ሚያዚያ 22 እውቅና የሚሰጥበት ሲሆን በሃገራችን ታሪክ ከፍተኛ ዝናና ታሪክ ያላችውን አትሌቶች እውቅና የምንሰጥበት ነው።
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ አትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ብቻ አይደለም አንጋፋ አትሌቶች ያሉበትን ሁኔታ በማየት ድጋፍ ይሰጣል ይህ ተግባር የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ አሳይመንት ነው
የሕብረት ባንክ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ጽጌሬዳ ተስፋዬ በፊርማ ስነስርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር


👉በዚህ በተቀደስ አላማ ላይ ለመሳተፍ የህብረባንኩ የተለያዩ ሰራወችን ይሰራል ከዚህ ውስጥ ኮርፖሬቱ ማህበራዊ ሃላፊነት ለመወጣት የሚያደርገው አንዱ አካል ነው።
በተጨማሪም አላማው በጎ እና ወደፊትም መደገፍ ያለበት ስለሆነ ባንኩ ይህንን ለመከወን የመግባቢያ ሰነድ
ለመፈራረም አሰቧል ስለዚህ በጋራ ለውጥ እናመጣለን ለዚህ ስራ ሁሉም ባለድርሻ አካል ያቅሙን ቢያግዝ ጥሩ ነው ሲሉ ተናግረዋል

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.