በጅጅጋ ከተማ የተካሄደው የማራቶን ሪሌ ውድድር።
17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በ ጅግጅጋ ከተማ በወንዶች የተጀመረ ሲሆን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ክብርት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሳራ ሀሰን፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ ዮሐንስ እንግዳ፣ የሱማሌ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ መሐመድ አብዱራህማን አህመድ እና የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ዘርፍ ም/ል ሐላፊ የሆኑት መሐመድ መኸዲ እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ውድድሩን አስጀምረዋል።
▪️በውድድሩ የፍፃሜ መርሀ-ግብር 11 ክለቦችና 3 ክልሎች የተወጣጡ በጠቅላላው 84 አትሌቶች ተሳትፎ አድርገውበታል።
ውድድሩ ፍፃሜውን ሲያደርግ ከ1ኛ-6ኛ ለወጡት ሽልማት ሲካሄድ በውጤቱም መሰረት
▪️የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንደኝነት ውድድሩን በማጠናቀቅ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን
▪️ ኢትዮ/ኤሌክትሪክ ፣ ኦሮሚያ ፖሊስ ፣ መከላከያ ፣ ኢኮስኮ እንዲሁም የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከ2-6 ያለውን ደረጃ ይዘው ማጠናቀቃቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ሚካኤል ደጀኔ።