ፋሲል ከነማ ከአሰልጣኙ ጋር የነበረውን ውል አቋረጠ

ፋሲል ከነማ ከአሰልጣኙ ጋር መለያየቱ ይፋ ሆኗል።

▪️በፋሲል ከተማ ሰሞነኛ ውጤት ደጋፊዎቹ በአሰልጣኙ ላይ ቁጣቸውን ማሰማታቸውን ቀደም ብለን መዘገባችን ይታወሳል።

▪️የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማህበር ህዝብ ግንኙነት አቶ አማኑኤል በዚ ጉዳይ ላይ ለኢትዮ ማዕድ የሬዲዮ ፕሮግራም ሀሙስ ምሽት ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸው አይዘነጋም።

ካነሱት ሀሳብ ለመጥቀስ ያክል…

👉 የደጋፊዎችን ጥያቄ የደጋፊ ማህበሩ የማስተናገድ ግዴታ እንዳለበት እና ጥያቄያቸውን ከተወያዩበት በኋላ ለቦርዱ እንደሚያቀርቡ

👉 አሰልጣኝ ስዩም ለሰሩት ስራ ትልቅ ክብር እንዳለ አብራርተው ነበር።

▪️ኢትዮጵያን ስፖርት ዛሬ ማምሻውን አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከአሰልጣኝነት ወንበራቸው በስምምነት መውረዳቸውን ከአሰልጣኝ ስዩም ከበደ አረጋግጧል።

▪️ያለፉትን ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ዐፄዎቹን የተረከቡት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ቡድኑን የሊጉን ዋንጫ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ እንዲያነሳ ማስቻላቸው ይታወቃል።

▪️እንደምክንያት የተወሰደው የቡድኑ ወቅታዊ የውጤት ማጣት እንደሆነ ታውቋል። ከመሪው ቅ/ጊዮርጊስ ጋር ያላቸው የነጥብ ልዩነት 10 መሆኑ የውድድር ዘመኑ ገና ያላለቀ ቢሆንም  ቀድሞም ቢሆን የአሰልጣኙ ነገር የማይዋጥላቸው እና ፍጹም ሽንፈት አንፈልግም በሚሉ ደጋፊዎች የተየሳው አመጽ እየተቀጣጠለ ወደአመራሮቹ መምጣት ለአሰልጣኙ በፍጥነት መነሳት ምክኒያት መሆኑ ሰሞኑን የነበሩ እንቅስቃሴዎች ይመሠክራሉ ።

በአሰልጣኙም በኩል በደጋፊው የነበረው ጫና ሊያሰራቸው እንዳልቻለ እና ሰሞኑን አንድ ተመልካች በስቴዲየም ውስጥ  ለመደብደብ ባደረገው ሙከራ ደስተኛ እንዳልነበሩ የቅርብ ደጋፊዎቻቸው ከስንብቱ ቀደም ብለው ይናገሩ ነበር።

የፋሲል ከነማ አብዛኛው ተጨዋቾችና ቋሚ ተሰላፊዎች ውላቸው የተጠናቀቀ መሆኑ የፋሲል ከነማን ቀጣይ ጉዞ ከባድ የሚያደርገው እንደሚሆን ይገመታል።

▪️ፋሲል ከነማ በቀጣይ ማለትም የፊታችን እሮብ  በ18ኛው ሳምንት  ወራጅ ቀጠናው ላይ ከሚገኘው ጅማ አባጅፋር ጋር በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስቴዲየም ጨዋታውን የሚያካሄድ ይሆናል።

#ፈለቀ ደምሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.