ሲቲዎች በሜዳቸው ቀያዮቹን ሊቨርፑሎችን ይፋለማሉ ።
ዘ ሲቲዝንስ እየተባሉ ሚጠሩት ማንቸስተር ሲቲዎች በሜዳቸው ኤቲሀድ ስቴዲየም ቀያዮቹን ሊቨርፑሎችን ይጋብዛሉ።
▪️ ሁለቱ ቡድኖች ሜዳ ላይ ሲገናኙ አዝናኝ እና ሁሌም ታክቲካዊ ሽኩቻዎች የሚንፀባረቁበት መርሀ-ግብር ሲሆን አሁን ደግሞ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ያላቸው የነጥብ ልዩነት 1 ብቻ መሆኑ ለጨዋታው የሚሰጠው ግምት እና ትኩረት ይበልጥ እንዲያይል አድርጓል።
▪️ ሲቲ ከ ሊቨርፑል ጋር ያደረጉትን ያለፉትን 3 ጨዋታዎች ማሸነፉ እንደ ጠንካራ ጎን የሚያዩት ቢሆንም ጋርዲዮላ በጣም የሚፈትነኝ አሰልጣኝ ክሎፕ ነው ሲሉ መደመጣቸው ጨዋታው ከባድ እንደሚሆንባቸው ጠቁመዋል።
▪️ሁለቱ አሰልጣኞች 2017/18 የውድድር ዘመን ጀምሮ ባደረጓቸው 182 ጨዋታዎች ፔፕ 438 ነጥብ ሲሰበስብ ክሎፕ በበኩሉ 412 ነጥቦችን የሰበሰቡ ሲሆን በጨዋታ በአማካይ 2.4 እና ከዛ በላይ ነጥብ ይሰበስባሉ። ይህም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የራሳቸውን ቀለም እንዲሁም የራሳቸውን አሻራ ያሳረፉ የዘመናዊ እግርኳስ ነፀብራቅ የሆኑ አሰልጣኞች ናቸው።
▪️በብርቱ ፉክክራቸው 5 አመታትን ያስቆጠሩት ሁለት ክለቦች ዘንድሮም አንገት ለአንገት የተናነቁበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
▪️ከጨዋታው በፊት ጋርዲዮላ በሰጡት አስተያየት 🗣 ለክለባችን እድገት የሊቨርፑል ተፎካካሪነት በጣም ጠቅሞናል። በቴብል ቴኒስ ተሮጀር ፌዴረር ፣ የጆኮቪች እና የናዳል ፉክክር 20 አመትን አስቆጥሯል። እኛ ገና 5 አመታትን ነው በፉክክር ያለነው ቢሆንም ግን የርገን ክሎፕ እስካሁን ከገጠሙኝ አሰልጣኞች ፈታኙ እሱ ነው ብሏል።
▪️ጀርመናዊው የርገን ክሎፕ 🗣 በበኩላቸው ፔፕ ጋርዲዮላ የአለማችን ምርጡ አሰልጣኝ ነው። ሁሉም ሰው እግርኳስን እንዲወድ እና እግርኳስን የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲገኝ እንደ እሱ የለፋ እና የጣረ የለም ሲሉም ተደምጠዋል።
▪️የእሁዱ አመሻሽ ጨዋታ ለ50 ጊዜ የሚያገናኛቸው ሲሆን ማንቸስተር ሲቲ 20 ጊዜ በማሸነፍ የበላይ ነው። ሊቨርፑል 18 ጊዜ ሲያሸንፍ 11ጊዜ ተከባብረው በአቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል።
#ፈለቀ ደምሴ
በጣምም ደስ ይላል! በርቱልን ፈሌ ና ሚኪ!
ዮኒ ሳንጃው ከቤተል