በስፔን ባርሴሎና ኢትዮጵያዊያኑ ኃፍቱ ተክሉ እና ጫላ ረጋሳ አሸነፉ

በስፔን ባርሴሎና በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያኑ ኃፍቱ ተክሉ እና
ጫላ ረጋሳ አሸነፉ

👉በአለም የአትሌቲክስ አወዳዳሪ አካል አይ ደብል ኤፍ(IAAF) እውቅና የተሰጠው ይህ የግማሽ ማራቶን 21.92 ኪሎሜትሮችን የሚሸፍን ሲሆን በስፔኗ ባርሴሎና ከተማ በሁለቱም ፆታዎች ውድድሩን ተከናውኗል።

👉በተመሳሳይ በሴቶች በተካሄደው ውድድር የአለም የ5,000 ሜትር ሜዳሊያ ባለቤቷ እና በዚ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካፈለችው ኬንያዊቷ ማርጋሬት ኪፕኬምቦይ 1:05:26 በመግባት ቀዳሚ ስትሆን

 

ኢትዮጵያዊቷ ጌጤ አለማየሁ 1:06:37 በመግባት ሁለተኛ እንዲሁም ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አስናቀች አወቀ 1:09:34 በመግባት 3ኛ በመሆን አሸንፈዋል።

👉በወንዶች ዘርፍ ኢትዮጵያዊው ሀፍቱ ተክሉ 59:06 በመግባት ቀዳሚ ሲሆን 4 ሰከንዶች ብቻ በመዘግየት ሌላው ኢትዮጵያዊ ጫላ ረጋሳ 59:10 በመግባት ሁለተኛ በመሆን ሲያሸንፉ።

 

ኬንያዊው ኤልቪስ ቼቦይ 59:15 ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ሌሎች በውድድሩ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ማለትም አንተነህ ዳኛቸው እና ክንዴ ደረሰ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ አረንጓዴው ጎርፍን አስታውሰዋል።

#ፈለቀ ደምሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.