ኢትዮጵያውያኑ ጀግኖች በሰርቢያ የሀገራቸውን የበላይነት አስጠብቀዋል

▪️በሰርቢያ ቤልግሬድ የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችን ወርቅ ፣ ብር እና ነሀስ ለሀገራቸው አስገኝተዋል።

▪️ሰንደቅ አላማችንን በቤልግሬድ ከፍ ብሎ እንዲታይም አድርገዋል።

👉በትናንትናው እለት የ1,500ሜ. የሴቶች የማጣሪያ ምድባቸውን ያለፉት አትሌቶቻችን
▪️ጉዳፍ ፀጋይ
▪️አክሱማዊት እምባዬ እንዲሁም
▪️ሒሩት መሸሻ ኢትዮጵያን ወክለው ከደቂቃዎች በፊት ተወዳድረዋል።

በውድድሩም ተጠባቂ የነበረችው ጉዳፍ ፀጋዬ አሁንም ድንቅ እንቅሰቃሴ በማሳየት 3:57:19 በመግባት የቦታውን ምርጥ ሰአት በማስመዝገብ በአንደኝነት ውድድሯን አጠናቃለች።

▪️አክሱማዊት እምባዬ 4:02:29 በመግባት 2ኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ እንዲሁም ሂሩት መሸሻ 4:03:39 ተከትላ በመግባት ለሀገሯ የነሀስ ሜዳሊያ አስመዝግባለች።

👉ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከ 1-3 በመውጣት ለሀገራቸው ወርቅ ፣ ብር እንዲሁም ነሀስ ማስመዝገብ ችለዋል።

#ፈለቀ_ደምሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.