አሰላ እየተካሄደ የሚገኘው የታዳጊዎች እና ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር።

የ2ኛው ቀን ያስቆጠረው እና አሰላ ላይ እየተካሄደ የሚገኘው 10ኛው ከ 20 አመት በታች እንዲሁም 3ኛው ከ 18 አመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ከማለዳው 2:00 ላይ በሴቶች ከፍታ ዝላይ ከ20 አመት በታች፣ በወንዶች ዲስከስ ውርወራ ከ18 አመት በታች ፣ በወንዶችና በሴቶች 3000 ሜ ከ20 አመት በታች ግማሽ ማጣሪያ ተጀምሯል።

▪️ሌላው ውድድር ከ18 አመት የሴቶች ዲስከስ ውርወራ ሲሆን አሸናፊዎቹም

1ኛ የኔ ሰው ያረጋል፣ ከአማራ ክልል፣ 35.15 ሜትር
2ኛ ትጓደድ ተሰማ ፣ ከአ/አ/ዮ፣ 33.95 ሜትር
3ኛ ማሪቱ አለባቸው፣ ከአማራ ክልል፣ 33.02 ሜትር

▪️ከ18 አመት በታች የወንዶች ከፍታ ዝላይ፣

1ኛ ኦኬሎ ኡጂሉ፣ ከኢት/ስፖ/አካዳሚ፣ 2.00 ሜ
2ኛ ገመዶ አባተ፣ ከጥሩነሽ ዲባባ፣ 1.90 ሜ
3ኛ ሳም ኡቻን፣ መከላከያ፣ 1.90 ሜ በሆነ ዉጤት አሸንፈዋል።

▪️ከ20 አመት በታች 3000 ሜትር ወንዶች በተካሄደው ውድድር

1ኛ አብዲሳ ፈይሳ ኦሮሚያ ክልል፣ 8:06:20
2ኛ ገበየሁ በላይ፣ ኦሮ/ፖሊስ፣ 8:06:64
3ኛ መልስ ብርሃኑ፣ አማራ ክልል፣ 8:07:74 በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

▪️በሴቶች ዘርፍ  ከ20 አመት በታች ከፍታ ዝላይ በተካሄደ ውድድር

1ኛ ኞፒክ ማጂ፣ ኢት/ኤሌክትሪክ፣ 1.70 ሜትር
2ኛ ፒሪያንክ ኛት፣ ሲዳማ ቡና፣ 1.68 ሜትር
3ኛ ኛጌም ፑል፣ ሲዳማ ቡና፣ 1.65 ሜትር

▪️በወንዶች ከ18 አመት በታች በተካሄደ ዲስከስ ውርወራ

1ኛ አቢቹ ገመቹ፣ ኦሮሚያ ክልል፣ 46.86 ሜትር
2ኛ በልስቲ እሸቴ፣ አማራ ክልል፣ 41.18 ሜትር
3ኛ በሃይሉ ጌትነት፣ አማራ ክልል፣ 40.74 ሜትር በመዝለል አሸንፈዋል።

▪️በወንዶች ከ20 አመት በታች በተካሄደ አሎሎ ውርወራ ውድድር

1ኛ ነናዊ ጊንደቦ፣ መከላከያ፣ 16.12 ሜትር
2ኛ ቦቃንዳ ፍሪሳ፣ ኢት/ን/ባንክ፣ 15.68 ሜትር
3ኛ ኤፍሬም ጉደሬ፣ ኦሮ/ፖሊስ፣ 14.55 ሜትር በመወርወር አሸናፊ ሆነዋል።

▪️ውድድሩ ነገም ሲቀጥል ዝላይ ፣ ዲስክ ውርወራ እንዲሁም መሰናክልን ጨምሮ በርካታ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.