ከ2 አመት ቆይታ በኋላ በተመለሰው የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊው ማ ይሆን?
▪️በ2020 መጋቢት ወር ጀምሮ መካሄድ ያልቻለው ይህ በማራቶን ዘርፍ ትልቅ ግምት የሚሰጠው የቶኪዮ ማራቶን ዘንድሮ ወደ ከ25,000 በላይ አትሌቶችን በማሰተፍ እንደሚካሄድ ተረጋግጧል። ለመጨረሻ ጊዜ ሲካሄድ አሸናፊ የነበረው ኢትዮጵያዊው ለገሰ ብርሀኑ ዘንድሮም ያን ገድል ለመድገም ይሮጣል።
▪️2:02:55 በመግባት የአለማችን 4ኛው ፈጣን ሰአት አስመዝጋቢው ሞስነት ገረመው ከነገ በስቲያ በሚካሄደው የማራቶን ውድድር ሌላው ግምት የተሰጠው ተፎካካሪ አትሌት ነው።
▪️ሁለቱም ኢትዮጵያዊያን ከኬንያዊው የአለም ሪከርድ ባለቤት ኤሊውድ ኪፕቾጌ ብርቱ ፉክክር እንደሚገጥማቸው አያጠያይቅም።
▪️የ2 ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ እንዲሁም በ2018 የበርሊን የማራቶን 2:01:39 በመግባት የአለምን ሪከርድ በእጁ ያስገባው ይህ የ37 አመት ኬንያዊ አላማውን ቀደም ብሎ ግልፆ ማድረጉ ይታወሳል። ይህም አለማችን ላይ ያሉትን እና ትልቅ ግምት የሚሰጣቸውን 6ቱን የማራቶን መድረኮች ማሸነፍ ሲሆን እስካሁን በበርሊን ፣ ቺካጎ እና ለንደን ማራቶን ማሸነፍ የቻለው ኪፕቾጌ ከነገ በስቲያ የሚካሄደውን የቶኪዮ ማራቶን ጨምሮ የቦስተን እና የኒውዮርክ ማራቶን ማሸነፍ ግቡ እንደሆነ ማሳወቁ ይታወቃል።

▪️በሴቶችም ባሳለፍነው አመት 2:14:04 ገብታ የአለም ሪከርድን መቆጣጠር የቻለችው ኬንያዊቷ ብሪጅድ ኮሴጊ በሴቶች አሁንም ቅድሚያ ግምት የተሰጣት አትሌት ስትሆን ሌላዋ ኬንያዊቷ አንግላ ታኑዪ እና ኢትዮጵያዊቷ አሸቴ በከሬ እና ህይወት ገ/ኪዳን ብርቱ ፉክክር እንደሚገጥማት ይጠበቃል።
ፈለቀ ደምሴ።
