ጉዳፍ ፀጋይ አስደናቂ ውጤት በኮፐርኒከስ።

▪️ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋዬ ከ 4 ቀን በፊት በፈረንሳይ ከተማ ሊዬቪን በተካሄደው 1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር 4:21:72 በመግባት 1ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወቃል።አምና በዚችው ከተማ 3:53:09 በመግባት የአለምን ሪከርድ በእጇ ማስገባቷ ሚታወስ ነው። አሁን ከ 4 ቀናት በኋላ በፖላንድ ፣ ኮፐርኒከስ በተካሄደው የ1500 ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ 3:54:77 በመግባት በአንደኝነት ውድድሯን አጠናቃለች። የገባችበት ሰአት ሁለተኛው ፈጣን ሰአት ሲሆን የቦታውንም ሪከርድ በእጇ ያስገባችበት መንገድ ፈጥራለች። በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ፍረወይኒ ሀይሉ እና ሀብታም አለም የራሳቸውን የግል ሰአት ማስመዝገብ ችለዋል።

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.