የሉሲዎቹ ተተኪዎች የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል።

በኮስታሪካ አዘጋጅነት ዘንድሮ ለ10ኛ ጊዜ የሚካሄደው ከ20 አመት በታች ሴቶች የአለም ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ከ2ዐ አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በ4ኛው ዙር ከ ታንዛኒያ አቻው ጋር የመልስ ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አካሂዶየመጀመሪያ ዙር ከ ሳምንት በፊት ወደ ዛንዚባር አቅንቶ 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት መሸነፉ ይታወሳል። ዛሬ የመልስ ጨዋታውን አካሂዶ 2-0 በሆነ ውጤት አሸንፈው የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል። እውነት ለመናገር ያን ያህል ትኩረት የማይሰጠው የሴቶች ከ20 አመት በታች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ከአስደናቂ ብቃት ጋር ውጤቱን በመቀልበስ በድምር ውጤት 2-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ቡሩንዲዋ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሱዋቪስት በመራችው ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ረድኤት አስረሳኸኝ ባስቆጠረችው ግብ 1-0 እየመራ ለእረፍት የወጣ ሲሆን ከእረፍት መልስ በተወሰነ መልኩ ተቀዛቅዞ ታይቷል። አሰልጣኝ ፍሬው ሀ/ገብርኤል በአጠቃላይ 3 ንም ቅያሪዎች ተጠቅሟል 1 አስገዳጅ ቅያሪም አድርጓል። በ81ኛው ደቂቃ ላይ የማዕዘን ምቱን ለማዳን የወጣችው የታንዛኒያዋ ግብ ጠባቂ አሻ ምሪሾ ስታው 16 ከ 50 ላይ በተጠንቀቅ ስትጠብቅ የነበረው ረድኤት አስረሳኸኝ ለራሷም ለቡድኑም ሁለተኛ ግብ ከመረብ አሳርፋለች። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም በድምር ውጤት 2-1 ማሸነፍ ችሏል።

በቀጣይ ከ ጋና ብሄራዊ ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ ብቻ የሚጠብቀው ሲሆን እሱን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻሉ በቀጥታ ለኮስታሪካው የአለም ዋንጫ ቲኬት ይቆርጣሉ።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.