ሪከርዶቹ የተሻሻሉበት የሂውስተን ማራቶን።

50ኛው አመታዊ ቼቭሮን ሂውስተን ማራቶን እንዲሁም ግማሽ ማራቶን ትላንትና በአሜሪካ ተካሂዷል። በሴቶች አሜሪካዊቷ ኬይራ ዲማቶ አሸናፊ ሆናለች። ከ 2005 በኋላም የሂውስተን ማራቶን ያሸነፈች የመጀመሪያዋ አሜሪካዊትም ሆናለች። የ37 አመቷ ኬይራ ዲማቶ የኮሌጅ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ ከ ሩጫው አለም ራሷን ማራቋ ይታወሳል። ከ8 አመት በኋላም ወደዚህ መድረክ ስትመለስ የሁለት ልጆች እናት ሆና ነው። ይህም ቢሆን ግን የአለም ሪከርድን ከማሻሻል አላስቆማትም። እ.ኤ.አ በ2006 የለንደን ማራቶን በዳና ካስተርን ተይዞ የነበረውን 2:19:36 በ24 ሰከንድ በማሻሻል 2:19:12 በመግባት አስደናቂ ውጤት አስመዝግባለች።

ኢንግሊዛዊቷ አሊስ ራይት እና አሜሪካዊቷ ማጊ ሞንቶያ በተመሳሳይ 2:29:08 በመግባት ተከታትለው 2ኛ እና 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል። በውድድሩ ተጠብቃ የነበረው እና የሁለት ጊዜ የቺካጎ ማራቶን አሸናፊዋ አፀደ ተሰማ 2:32:38 በመግባት 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ይህን ውድድር ከዚ በፊት ማለትም ከ2007 አንስቶ 10 የተለያዩ ኢትዮጵያዊያያአትሌቶች እየተፈራረቁ ማሸነፍ ቢችሉም ዘንድሮ ግን ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ምስራቅ አፍሪካ ወክላ ማለት ይቻላል አፀደ ተሰማ 5ኛ ደረጃን ይዛ ነው ውድድሯን ማጠናቀቅ የቻለችው።

▪️በወንዶች ኬንያዊው ጄምስ ንጋንዱ 50ኛው አመታዊ የ ቼቭሮን ሂውስተን ማራቶን አሸናፊ መሆን ችሏል። የመጀመሪያ የማራቶን ሩጫ ተሳትፎውን ማድረግ የቻለው ጄምስ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2:11:03 ፈጅቶበታል። ፀሎት እና ደስታውንም ከታች እንደምትመለከቱት ለጥቂት ደቂቃዎች ተንበርክኮ በመቆየት አሳይቷል ።
▪️ ከ7 ሰከንድ በኋላም ባህሬናዊው አብዲ አብዶ 2ኛ ሆኖ ገብቷል።
▪️ሌላው ኬንያዊው አሌሺያ ባርኖ 2:11:16 በመግባት 3ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ይህን ውድድር አምና በአንደኝነት ያጠናቀቀው ከልክሌ ገዛኸኝ 2:11:20 በመግባት 5ኛ ሆኖ አጠናቋል።

ይህ ውድድር መግቢያችን ላይ እንዳልነው ግማሽ ማራቶንም ያካተተ ነው። 21 ኪሎሜትሮችን የሚሸፍነውን የግማሽ ማራቶን ትላንት በሂውስተን ቴክሳስ ተካሂዷል። በሴቶች ኬንያዊቷ ቼፕጌኖ አሸናፊ መሆን ችላለች። ከ 2 ወር ባልሞላ ጊዜ በፊት በፊላደልፊያ 1:07:22 የገባችው የ 28 አመቷ ቼፕጌኖ ትላንት ደግሞ 1:05:03 በመግባት የራሷንም የአለምንም ሪከርድ አሻሽላለች።ይህ የገባችበት ሰአት በአሜሪካ አፈር የመጀመሪያው ፈጣን ሰአት ነው።ከዚ በፊት ሪከርዱ በ2019 በኬንያዊቷ ብሪጅድ ኮሴጊ 1:05:50 ተይዞ እንደነበር ይታወሳል።

▪️አሜሪካዊቷ ሳራ ሆል 1:07:15 በመግባት 2ኛ ስታጠናቅቅ በ2018 በሌላዋ አሜሪካዊ ሞሊ ኸድል ተይዞ የነበረውንም ሪከርድ ማሻሻል ችላለች። በአሜረመካ ፈጣኗ የግማሽ ማራቶን ሯጭ መባልም ችላለች።
▪️ስካት 1:07:32 በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

▪️በወንዶች ለመጀመሪያ ጊዜ የሂውስተን ቴክሳስ ማራቶን የተሳተፈው ሚልኬሳ መንገሻ ቶሎሳ አሸናፊ ሆኗል። የ21 አመቱ ሚልኬሳ መንገሻ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 1:00:24 የፈጀበት ሲሆን ጥሩ ትንቅንቅ ከኬንያዊው ጆን ኮሪር ጋር አድርገው ነበር። የመጨረሻዎቹ 2 ኪሎሜትሮች ላይ ሚልኬሳ ነጥሮ እና ፈጥኖ በመውጣት አሸናፊ መሆን ችሏል።

▪️ኬንያዊው ጆን ኬሪር 3ሰከንዶችን ብቻ ዘግይቶ 2ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሌላው ኬንያዊ ዊልፈርድ ኪሚትዪ ከ 1 እስከ 3 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.