ለመጀመሪያ ጊዜ በአዳማ ከተማ የተካሄደው “ሄማ-ሬስ ሩጫ።
▪️’ሄማ ሬስ’ አዲስአበባ ኢንተርናሽናል ግማሽ ማራቶን
#NOMORE ወይም በቃ ቨሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ፣ በአዳማ ፣ በባህርዳር ፣ በሀዋሳ ፣ በድሬዳዋ ፣ በጅጅጋ ፣ በሀረር ፣በአርባምንጭ ፣ በሰመራ ፣ በአሶሳ ፣ በጋምቤላ እና በቦንጋ ከተሞች የሚያደርገውን የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ዛሬ በአዳማ ከተማ ከ 30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉበት እንዲሁም ከ 500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሮጡበት ውድድር ሲሆን ከ 1 እስከ 3 ለወጡ አትሌቶች ሜዳላያ እና ዳጎስ ያለ የሽልማት ገንዘብ ተዘጋጅቷል።እንዲሁም ሽልማቱ እስከ 10ኛ ድረስ ለወጡ አትሌቶችም ሚቀጥል ሲሆን ፤ ከውድድሩ የሚገኘው ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ የሚውል ታላቅ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ሆኖ በታሪክ መዝገብ ይሰፍራል። አዲስአበባ እና ዙሪያዋ ለሚገኙ ወደ አዳማ አቅንተው “ሄማሬስ” የሩጫ ውድድርን መሳተፍ ለሚፈልጉ አትሌቶች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎትም አዘጋጅተዋል።
ውድድሩ አሁን ከደቂቃዎች በፊት ሲጠናቀቅ በሴቶች
▪️መድን ኢሳ ከ አማራ ክልል ማረሚያ
▪️መብራት ግደይ ከኮልፌ ቀራኒዮ ክለብ 2ኛ እንዲሁም
▪️ህብስት ጥላሁን ከመከላከያ 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
▪️ጌጤ አለምአየሁ ከ ኦ.ሲ.ኢሲ
▪️ቤተልሄም አፈንጉስ ከ አማራ ማረሚያ
▪️ደበሽ ከለለ ከ ንግድ ባንክ
▪️በቀለች ተኩ በግል
▪️ራሂማ ቱሳ ከአዳማ ክለብ
▪️አስማረች ነጋ በግል ከ 4-9 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
በወንዶች 10 ኪሎ ሜትሩን
▪️ቦክ ድሪባ ከ ለገጣፎ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ
▪️ተስፋሁን ከ መከላከያ 2ኛ ሲሆን
▪️ደበበ ተካ ከማረሚያ 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
▪️አደለደለው ማሞ በግል
▪️ምትኩ ጠፋ ከአሰላ
▪️ገብርኤል እርቅይሁን በግል
▪️ገብሩ ንጉሴ በግል
▪️አዲሱ ነጋሽ ከ ማረሚያ
▪️መንግስቱ በቀለ ከ 4 እስከ 9 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
በወንዶቹ 10 ኪሎሜትር ውድድር ላይ አንድ ነገር ተፈጥሯል እሱም በቴዎድሮስ ጥላሁን የሚሰለጥን አንድ አትሌት ውድድሩን ለመጨረስ እየመራ በግምት 12 ሜትር ሲቀረው የወደቀ አትሌት ነበር። ግን ሞራሉን ለመጠበቅ በማሰብ ስቴጅ ላይ ከተሸላሚዎቹ ጋር ወቶ እውቅና እንዲያገኝ እና የ 5,000 ብር ሽልማትም ተበርክቶለታል።
ፈለቀ ደምሴ።