የአለም ክብረ-ወሰን የተሰበረበት የቫሌንሺያዉ 10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ።
▪️በወንዶች ኬንያዊው ሮኔክስ ኪፕሩቶ ትላንትና በስፔኗ ቫሌንሺያ የተካሄደው የ 10 ኪሎሜትር ሩጫ 26:24 በመግባባት አሸናፊ መሆን ችሏል።
የ10,000ሜትር ነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚው ኪፕሩቶ ገና 20 አመቱ ሲሆን ከ6 ሳምንት በፊት በዚህቹ ከተማ ኡጋንዳዊው ጆሸዋ ቼፕቴጊ ተሻሽሎ የነበረውን እና የትራክ ላይ ክብረ-ወሰን ከነበረው 26:11
14 ሰከንድ በመዘግየት ኪፕሩቶ 26:24 የገባ ሲሆን የአለም ክብረ-ወሰን በጎዳና ላይ ሩጫ ሪከርድ ባለቤት እንዲሁም የግሉ ምርጥ ሰአት ሆኖ ተመዝግቦላታል። ሌላው ኬንያዊ benard kimeli 27:12 በመግባት 2ኛ ሲሆን ስዊዘርላንዳዊው julien wanders 1 ሰከንድ በመዘግየት 27:13 በመግባት 3ኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል።
በሴቶች የኬንያዊውኑ ሮዝመሪ ዋንጅሩ ፣ ኖረም ጄሩቶ ፣ ቼፕኪሩዪ መካከል የተደረገው ፉክክር አዝናኝ ነበር።የመጨረሻዎቹ 2 ኪሎሜትሮች ላይ የ 29 አመቷ ሼላ ቼፕኪሩዪ ነቅላ በመውጣት ጠንካራነቷን አሳይታ 29:46 በመግባት በአንደኝነት አጠናቃለች።በዚህ የ10 ኪሎሜትር ርቀት ዘርፍ ውስጥ የአለማችን 2ኛ ፈጣኗ ሴት ያደርጋታል። ሮዝመሪ ዋንጅሩ እና ኖራህ ጄሩቶ በእኩል 29:51 በመግባት 2ኛ እና 3ኛ ወተዋል። ኢትዮጵያዊቷ ቦሰና ሙላቴ በ 30:50 በመግባት 4ኛ ስታጠናቅቅ ሌላዋ ኢትዮጵያዊ ረድኤት ዳንኤል 31:55 በመግባት 6ኛ በመሆን ውድድሯን አጠናቃለች።
ፈለቀ ደምሴ።