አመታዊው የካምፓቺዮ ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደምቀው ታይተዋል።
▪️በጣልያኗ ሳን ጆርጂዮ ሌጋኖ የተካሄደው አመታዊው የካምፓቺዮ ሩጫ ላይ ኢትዮጵያዊያኑ ይሁኔ አዲሱ እና ዳዊት ስዩም በሁለቱም ፆታ ድል መጎናፀፍ ችለዋል። ይህ ውድድር ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ ሚካሄዱ ሲሆን ከዚ በፊትም ሀይሌ ገ/ስላሴ ፣ ቀነኒሳ በቀለ ፣ ኢማና መርጊያ ፣ እና ሙክታር እድሪስ ከዚ በፊት ይህን ታላቅ ውድድር ያሸነፉ አትሌቶች ናቸው።
▪️ጠንካራ ፉክክር የታየበት የሴቶች ውድድር 4 ኪሎሜትር ሲቀረው 7 ሯጮች ብቻ ወደፊት በመምጣት ሲፎካከሩ ነበር። ግን ውድድሩ ሊጠናቀቅ 500 ሜትሮች ሲቀሩት ዳዊት ስዩም ፣ ቢያትሪስ ቼቤት እና ራሄል ገ/ዮሀንስ ነቅለው በመውጣት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ አካሂደዋል።ግን ኢትዮጵያዊቷ ዳዊት ስዩም 18:48 በመግባት አሸናፊ መሆን ችላለች። ዳዊት በዚሁ በጣልያን Bolzano ግዛት ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ለት 5 ኪሎሜትር የመንገድ ላይ ሩጫ ማሸነፉ ይታወሳል። ከዳዊት 1 ሰከንድ ብቻ በመዘግየት ኤርትራዊቷ ራሄል ዳንኤል ገ/ዮሀንስ በ 18:49 2ኛ ስትጨርስ ከ 2ሰከንድ በኋላ ኬንያዊቷ ቢያትሪስ ቼቤት በ 18:51 3ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል።
▪️በወንዶቹ አዲሱ ይሁኔ 28:39 በመግባት በአንደኝነት አጠናቋል። መጋቢት ወርላይ 19 አመቱን የሚይዘው አዲሱ ይሁኔ ከ 20 አመት በታች የአለም ሻምፒዮና ላይ በ 5000 ሜትሩ የግሉን ምርጥ ሰአት 12:58:98 መግባቱ ይታወሳል። ”ሩጫውን እንደማሸንፍ ሙሉ እምነት ነበረኝ ለዚህም በደንብ ከአትሌት ሰለሞን ባረጋ ጋር በመሆን ተዘጋጅቼ ነበር ስላሸነፍኩ ደስ ብሎኛል” ብሏል።
ኬንያውያኑ አትሌቶች ከ 2-4 ያለውን ደረጃ ይዘው ሲያጠናቀዋል
ኮነር ኪፕላጋት እና አሞስ ሳሬም በ 8 ሰከንድ ተለያይተው 28:45 እና 28:53 ተከታትለው ገብተዋል።
ኤርትራዊው አሮን ክፍሌ 5ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
ፈለቀ ደምሴ።