በቢሾፍቱ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ።
የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ ‘ለሀገሬ ሰላም እሮጣለሁ’ በሚል መሪ ቃል በትላንትናው እለት በቢሾፍቱ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በእለቱ በክብር እንግዳነት የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ክቡር አቶ ቀጀላ መርዳሳ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ፣ ኮማንደር አትሌት ማርቆስ ገንቲ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ገዛኸኝ አበራ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በእለቱ የተገኙ ሲሆን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አለምአየሁ አሰፋ በእለቱ ለተገኙ ታዳሚያን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል። ውድድሩ 10 ኪሎሜትሮችን የሸፈነ ሲሆን ጠዋት 2:00 ሲል ውድድሮቹ ጀምረዋል።
በሴቶች በተካሄደው ውድድር
▪️ግርማዊት ገ/እግዚአብሔር ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ
▪️ብርቱካን ወልዴ እንዲሁም ጥሩዬ መስፍን በግል 2ኛ እና 3ኛ አጠናቀዋል።
▪️አይናዲስ መብራት ከኢትዮ ኤሌትሪክ 4ኛ
▪️አንችንአሉ ደሴ ከፌዴራል ማረሚያ 5ኛ
▪️ፍቅርተ ወረታ ከመከላከያ 6ኛ
▪️አበራሽ መናስቦ ከኢትዮ ኤሌትሪክ 7ኛ
▪️አዲስ ተሾመ ከኢትዮ ኤሌትሪክ 8ኛ በመሆን አጠናቀዋል።
በወንድ አትሌቶች ደግሞ
▪️ገመቹ ዲዲ ከኢትዮ ኤሌትሪክ 1ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ
▪️አንተንአየሁ ዳኛቸው ከመከላከያ 2ኛ ሆኖ ውድድሩን ጨርሷል።
▪️ሲሳይ ፍቃዱ ከገመዶ ማኔጅመንት 3ኛ
▪️ባዘዘው አስማረ ከመርሻ ማኔጅመንት 4ኛ
▪️አብዱ አስፋው ከይረፋ ማኔጅመንት 5ኛ
▪️ሀብታሙ አባዲ ከኢትዮ ኤሌትሪክ 6ኛ
▪️በረከት ነጋ ከገመዶ ማኔጅመንት 7ኛ
▪️ኡስዲን መሀመድ ከመከላከያ 8ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በሁለቱም ፆታዎች የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ስፖርት ክለብ በአንደኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።
የኢትዮጽያ አትሌቶች ማህበር ውድድሩን ሲያዘጋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢሆንም ግን የመጀመሪያውየማይመስል የተዋጣለትፕሮግራም ነበር።በአጠቃላይ ማህበሩ ከፕሬዚዳንት እስከ ታች ያሉ አባላቶች ጋር መናበብ የታየበት ለሌሎች ዝግጅቶችም ምሳሌ ሚሆን ሚችል ውድድር ነው።ለውድድሩ መሳካት የተለያዩ አባላት ላበረከቱት አስተዋፅኦ የምስክር ወረቀት በኮማንደር አትሌት ማርቆስ ገንቲ ተበርክቶላቸዋል። እንዲሁም የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ለውድድሩ እና ለዝግጅቱ መሳካት ለነበረው የጎላ ሚና የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል።
ሚካኤል ደጀኔ።