ዋልያዎቹ ይፋዊ የሽኝት ፕሮግራም ተካሄደ።

▪️የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸው እና የፊታችን ጥር 1 የመጀመሪያ ጨዋታውን እንደሚያካሄዱ ይታወቃል። ለዚህም ትልቅ መድረክ ወደ ሚዘጋጅበት ሀገር ካሜሮን ዋና ከተማ ያውንዴ ነገ ያቀናል። በዚህም መሰረት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት በskylight ሆቴል ዛሬ ምሽት ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

▪️አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አምበሉ ጌታነህ ከበደ እንዲሁም ቡድን መሪው አቶ አበበ ገላጋይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከስፓርት እና ባህል ሚኒስቴር አቶ ቀጀላ መርዳሳ እና ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አቶ ኢሳያስ ጅራ እጅ ተረክበዋል። እንዲሁም ፌዴሬሽኑ ለአጋሮቹ እና ለመንግስት ባለድርሻ አካላት የማስታወሻ ስጦታዎችን አበርክቷል።ከዚህ በተጨማሪ አቶ ኢሳያስ ጅራ ባደረጉት ብሄራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ ከቻለ የ9 ሚሊዮን ብር ማበረታቻ ሽልማት እንደሚበረከትለት ይፋ አድርገዋል።

ሚካኤል ደጀኔ።

ፎቶ ምንጭ
ሶከር ኢትዮጵያ

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.