የፖላንዱን አለም አቀፍ የሀገር ውስጥ አትሌቲክስ ማን ያሸንፍ ይሆን?

▪️ከ አንድ አመት በፊት በፈረንሳይ ሊዮቪን ከተማ በተደረገ የ 3000 ሜትር ሩጫ ሶስቱ ማለትም ጌትነት ዋሌ ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ለሜቻ ግርማ ከ 1 እስከ 3 ድረስ ማሸነፋቸው ይታወሳል። አሁንም በዛው በተመሳሳይ ርቀት በፖላንድ ቶሩን ከተማ በሚደረገው የcopernicus cup የፊታችን የካቲት 13 ውድድራቸውን ያካሄዳሉ።

▪️በ 3000 ሜትር መሰናክል ሩጫ ሚታወቀው ጌትነት ዋሌ አመቱ የጀመረ አካባቢ በኬንያዊው daniel komen’s ለረጅም ጊዜ ተይዞ የነበረውን የ 3000 ሜትር የሀገር ውስጥ ሪከርድ ማለትም 7:24:90 በ8 ሰከንዶች ብቻ በመዘግየት 7:24:90 በመግባት ማሸነፉ ይታወሳል።ከዛም ሰለሞን ባረጋ 7:26:10 በመግባት 2ኛ ሲጨርስ ለሜቻ ግርማ 7:29:24 3ኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቁ ይታወሳል።እንዲሁም ሌላው ኢትዮጵያዊ በሪሁ አረጋዊ 7:29:24 6ኛ ሆኖ አጠናቆ ነበር። የነዚህ አትሌቶች ፉክክር ዳግም ሚጠበቅ ነው። በcopernicus cup የካቲት 13 ፖላንድ ምጠብቃቸው ይሆናል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.