በባህሬን የተካሄደው ግማሽ ማራቶን

▪️ትላንት በተካሄደው የባህሬን ግማሽ ማራቶን የ 26 አመቷ ጎይቶም ገ/ስላሴ የግሏን ምርጥ ሰአት 1:05:36 በመግባት በአንደኝነት አጠናቃለች። በመስከረም ወር በበርሊን 2:20:09 በመግባት ካሸነፈች በኋላ ያሳካችው ድል ነው።

▪️የኦሎምፒክ የ 10,000 ሜትር ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው ለባህሬን የምትሮጠው ቃልኪዳን ገዛኸኝ በ ጎይቶም ገ/ስላሴ ተቀድማ 11 ሰከንዶችን ዘግይታ 2ኛ ሆና አጠናቃለች። ኬንያዊው ሼይላ ኪፕሮቲች 1:07:01 በመውጣት 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

▪️በወንዶች ሙሉ ለሙሉ የኬንያውያን የበላይነት የተንፀባረቀበት ውጤት ሲመዘገብ 1ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የኪፕሊሞ እና 2ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ኮሮስ ትንቅንቃቸው ተመልካችን ያዝናና ነበር ሁለቱም ኬናውያን በእኩል 1:00:01 ነው የገቡት ኢትዮጵያን ወክሎ በውድድሩ የተሳተፈው ጀማል ይመር 6ኛ ሆኖ ውድድሩን ቋጭቷል።

ሚካኤል ደጀኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published.