የኒውዮርክ ማራቶን ተካሄደ።

▪️የ2021 የኒው ዮርክ ማራቶን ዛሬ የተካሄደ ሲሆን የዘንድሮው ውድድር ሲካሄድ ለ50 ጊዜ ነው። 41 ኪሎሜትሮች ሚሸፍነው ይህ ትልቅ ማራቶን በኮቪድ ምክንያት የውድድሩ ተሳታፊዎችን ወደ 33,000 ቀንሷል።

▪️የአማችን ትልቁ የማራቶን ውድድር ዘርፍ ውስጥ ሚካተተው የኒውዮርክ ማራቶን ከ 1ሚሊየን በላይ ሚሆኑ ሰዎች በቀጥታ የቴሌቪዥን መስኮት የተከታተሉት ሲሆን እስከ 10,000 ሚሆኑ ተመልካቾች ከጎዳና ላይ ተገኝተው አትሌቶችን ሲያበረታቱ ታይተዋል።

▪️የአምናው የኒውዮርክ ማራቶን ኬንያዊያን ደምቀው ያመሹበት ነበር።በወንዶች ኬንያዊው ካምዎሮር 1ኛ ሆኖ ውድድሩን ሲያጠናቅቅ በሴቶችም ኬንያዊቷ ጄፕጎስጊ ውድድሩን በቀዳሚነት ማጠናቀቁ ይታወሳል።

▪️ኒውዮርክ ከፊል ደመናማ ሆና ስትውል ወበቃማ እና ሞቃታማ የአየር ፀባይ ይዛ ነበር ውድድሩን ያካሄደችው።

▪️በወንዶች ኬንያዊው አልበርት ኮሪር  2:08.22
1ኛ ሆኖ ሲጨርስ
ሞሀመድ ኤልአራቢ  2:09.06 2ኛ ሆኖ የገባበት ሰአት ነው።
ኢትዮጵያዊው እዮብ ፋኑኤል 2:09.56 3ኛ ሆኖ ጨርሷል።

▪️በሴቶች
ፔሬስ ጄፕቺርቺር በ 2:22.39 1ኛ ስትሆን
ቫዮላ ቼፕቱ በ  2:22.44 2ኛ ሆናለች
ኢትዮጵያዊቷ አባበል የሻነህ 2:22.50 3ኛ አጠናቃለች።

ሚካኤል ደጀኔ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.