የማንቸስተር ደርቢ።

▪️186ኛው የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ በኦልድትራፎርድ ሲካሄድ የፔፕ ጋርዲዎላው ማንቸስተር ሲቲ 2-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በ4 ማይል የሚለያዩት እነዚህ 2 ቡድኖች ድሮ በማንቸስተር ዩናይትድ የበላይነት ሚጠናቀቅ የነበረ እና የደርቢ ስሜቱ ወደ 1 ቡድን ያጋደለ የነበረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ከ10 አመት ወዲህ ማንቸስተር ሲቲ የአረቡ ሼክ መንሱር እጅ ከወደቀ በኋላ በተጫዋችም በአመራርም ባመጣው ለውጥ ማንቸስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ ተፎካካሪ እየሆነ መምጣት የቻለ ቡድን ሲሆን ይባስ ብሎም በደርቢ ጨዋታዎች እጅ ማይሰጥ ክለብ እየሆነ መጣ ስለዚህ እነዚህ 2 ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ አጎጊ እና ተጠባቂ እየሆነ መጥቷል።

▪️ጨዋታው በተጀመረ በ7ኛው ደቂቃ ላይ የሩፋኤልን ቫራን አለመኖር ተከትሎ እሱን ተክቶ የገባው አይቮሪኮስታዊው ኤሪክ ቤይሊ ራሱ ላይ አስቆጥሮ ሲቲ ቀዳሚ መሆን የቻለበት እድል ተፈጠረ በማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ላይም ራሱ ላይ ግብ ያስቆጠረ የመጀመረያው ተጫዋች ሆኗል።
▪️ ከዚች ጎል በኋላም ተጭኖ መጫወት የጀመረው የፔፕ ቡድን በ ኬቪን ዴብራይን እንዲሁም በጋብሬል ሄሱስ አማካኝነት ያለቀላቸው ሚባሉ ሙከራዎች ሳይቀር ዴቪድ ደኸያ ሲያመክናቸው ነበር። ግን ልፋቱን ገደል የከተተች ኳስ በ45ኛው ደቂቃ ላይ በጨዋታው ድንቅ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ፖርቹጋላዊው ጆአዎ ካንሴሎ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ የሉክ ሾ ስህተት ታግዞበት በሌላው ፖርቹጋላዊ በርናርዶ ሲልቫ አማካኝነት ሲቲ 2ኛ ጎል አስቆጠረ።
በርናርዶ ሲልቫ ኦልድትራፎርድ 4ጊዜ የመጫወት እድል ሲያገኝበ3ቱ ግብ ማስቆጠር ችሏል።በጨዋታው ድንቅ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ሌላው ፖርቹጋላዊ ጆአዎ ካንሴሎ የጨዋታው ኮኮብ በመባል ተመርጧል።

▪️የኦሌ ጎነር ሶልሼር ቡድን ከእረፍት መልስ ኤሪክ ቤሊን በጄደን ሳንቾ ግሪንውድን በራሽፈርድ ተክተው ውጤት ለማምጣት ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም።
በ 3-5-2 ፎርሜሽን ወደሜዳ የገባው የኦሌ ጎነር ሶልሼር ቡድን በተለይ የመጀመሪያ ጎሉን መስተናገደ በኋላ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ሲቸገሩ ተስተውሏል። 1የማዕዘን ምት ብቻ በጨዋታው ማግኘት የቻሉት ዩናይትዶች ወደጎል አላማቸውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ የቻሉትም 1ብቻ ነው።ከዚህ በፊት በሁሉም ውድድሮች ካደረጉት 12 ጨዋታዎች 6ኛ ሽንፈትም ሆኖ ተመዝግቧል። ኦሌ ጎነር ሶልሼር ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት የማንቸስተር ዩናይትድን መጥፎ የፕሪሚየር ሊግ ጉዞ ወደጥሩ መስመር ይቀየራል ሲል አስተያየቱን ሰቷል።

▪️ፔፕ ጋርዲዮላ ከነአጥቂ ችግሩ ማለትም በክረምቱ  በክለቡ ሪከርድ በሆነ ዋጋ ማንቸስተር ሲቲን የተቀላቀለው ጃክ ግሪሊሽ፣ስተርሊንግ የመሳሰሉ ተጫዋቾችን ሳይዝ ወደ ኦልድትራፎርድ አቅንቶ 3 ነጥቡን አሳክቶ ተመልሷል።

ሚካኤል ደጀኔ ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.