ማንቸስተር ዩናይትድ እና ውጤት ቀውስ።
▪️የኦሌ ጎነር ሶልሼሩ ማን ዩናይትድ ወደ ኪንግ ፓወር አቅንቶ የብሬንዳን ሮጀርሱን ሌስተር ሲቲ ጋር ጨዋታውን 11:00 ሲል አካሂዶ ነበር።ጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች ጥሩ እንቅስቃሴ የታየበት ነበር።
▪️ማንቸስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው 29 ጨዋታዎች ሽንፈት ሳይቀምስ ተጉዞ ነበር።የ ብሬንዳን ሮጀርስፈሱ ሌስተር ሲቲ 4-2 በሆነ የማሸነፊያ ውጤት ይህን ጉዞ ገቶታል።
▪️ታዳጊው ሜሰን ግሪንውድ በ19ኛው ደቂቃ ላይ ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ ቡድኑን መሪ አድርጋ የነበረ ቢሆንም ቤልጂየማዊው ዩሪ ቲሊማንስ የ ዴቪድ ዴኸሀ የአቋቋም ስህተት ተጠቅሞ የአቻነቷን ግብ በ 31ኛው ደቂቃ አስቆጥሮ ቡድኖቹ በ አቻ ውጤት የመጀመሪያው አጋማሽ አጠናቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል። ከእረፍት መልስ ተጭኖ ሲጫወት የነበረው የብሬንዳን ሮጀርሱ ሌስተር ሲቲ በቱርኩ ተከላካይ ካግላር ሶዩንቹ አማካኝነት መሪ መሆን ሚችሉበትን እድል ቢያመቻቹም መሪነታቸው ለ 4ደቂቃ ነበር የቆየው።እ.ኤ.አ November 2020 አምና ህዳር ወር ላይ ባጋጠመው ጉዳት ትከሻው ላይ ቀዶ ጥገና አድርጎ የነበረውና ዘንድሮ አንድም ጨዋታ ለቀያዮቹ ማድረግ ያልቻለው ዶ/ር ማርከስ ራሽፎርድ ቡድኑን አቻ ምታደርግ ኳስ ከመረብ አገናኝቷል።ይህች የአቻ ግብም መቀሸየት የቻለችው ለ 1ደቂቃ ነበር።ጄምስ ማዲሰንን ቀይሮ የገባው አዮዜ ፔሬዝ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ጄሚ ቨርዲ ባግባቡ ተጠቅሞ ቡድኑን ዳግም እንዲመራ አስችሏል።የጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ ኢህናቾን ተክቶ የገባው አጥቂው ፓትሰን ዳካ በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያውን ቡድኑ ደሞ መሪነቱን ወደ 4 ያሳደገ ኳስ ከመረብ አዋህዷል።
▪️ውጤቱ ኦሌ ጎነር ሶልሼር ላይ ጫና ሚያበዛ እና በማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ሶልሻየር ጨዋታ ሚመራበት መንገድ ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ አድርጎቸዋል።በቀጣይም ከባድ ጨዋታዎች ሲጠብቁት ከሊቨርፑል ፣ ቶተንሀም፣ ማንቸስተር ሲቲን ሚያገኝ ይሆናል።
ሚካኤል ደጀኔ