የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጫዋች እና አሰልጣኝ ይፋ ሆኗል።
▪️ በክረምቱ ጁቬንቱስን ለቆ ወደ ቀድሞ ክለቡ የተመለሰው የ36 አመቱ ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የወሩ ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመርጧል። ወደ ፕሪምየር ሊጉ ከመጣ ገና 1 ወሩ ቢሆንም ተፅዕኖ ፈጣሪነቱ እና በ ፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው 3 ጨዋታዎች 3 ግቦችን ማስቆጠሩ ይህን ክብር እንዲጎናፀፍ አስችሎታል።በ ፕሪሚየር ሊጉ ታሪክም 5ጊዜ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ክብርን ያገኘ 6ተኛው ተጫዋች ሆኗል።
▪️በ አሰልጣኞቹ ዘርፍም የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ስፔናዊው ሚኬል አርቴታ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ተብሎ ተመርጧል። በወሩ ካደረጋቸው 3 ጨዋታዎች 3ንም በማሸነፍ በ2ቱ ጨዋታ ደሞ መረቡን ሳያስደፍር በአንፃሩ ተጋጣሚዎቻቸው ላይ 5 ግቦችን እንዲያስቆጥሩ ምክንያት ሆኗል።የአርሰናል አሰልጣኝ ሆኖ ይህን ክብር ለመጨረሻ ጊዜ ያሳኩት እ.ኤ.አ በ 2015 ኦክቶበር ወር ላይ አርሰን ቬንገር ነበሩ።