አስገራሚው የቤልጄየም እና የፈረንሳይ ትንቅንቅ
ትላንት በተደረገው የኔሽንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ 1 ጨዋታ ቤልጂየም እና ፈረንሳይ’ን በ ጁቬንቱሱ ቱሩን ስቴዲየም የተካሄደ ሲሆን ክይንታዊ በሆነ መልክ ከኋላ ተነስተው የ ዲዲዬ ዴሻንፕ ብድኖች 3-2 በሆነ ውጤት ለ ዋንጫው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
የ ሮቤርቶ ማርቲኔዙ እና ለ 3 ተከታታይ አመታት የአለም ቁጥር 1 ሆና መቀመጥ የቻለችው ቤልጂየም ብሄራዊ ቡድን ከ እረፍት በፊት በ ካራስኮ⚽️ እና ሮሜሉ ሉካኩ⚽️ ድንቅ ግብ ታጅበው 2-0 አየመሩ ለ እረፍት ወጥተው ነበር።
የ ኋላ ኋላ ግን ውጤቱን ማስጠበቅ ሳይችሉ በ ካሪም ቤንዜማ⚽️
ኪሊያን ምባፔ ⚽️የ ፍፁም ቅጣት ምት ጎል አቻ መሆን ሲችሉ የጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ የ ኤሲ ሚላኑ ግራ መስመር ተከላካይ ቲዮ ሄርናንዴዝ 16 ከ ሀምሳው ጠርዝ ላይ አክርሮ የመታት ኳስ ኮረቱዋ መቆጣጠር ሳይችል መረቡን ላይ አርፋለች።
በዚህ ጨዋታ ፈረንሳይ ላይ በ 1 ጨዋታ ሁለት አሲስት ያደረገው ኬቨን ዴብራይን ከ ሊዮኔል ሜሲ ቀጥሎ ሁለተኛ ተጫዋች ያደርገዋል።
በዚህም መሰረት ስፔን ከ ፈረንሳይ ለዋንጫ ያለፉ ቡድኖች መሆናቸው እርግጥ ሆኗል።ሁለቱም ቡድኖች በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ለዋንጫ የደረሱት።